ካረካህ (Karekah) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 4.jpg


(4)

ይሆናል
(Yehonal)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 3:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

ምነው ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ አሃሃ ፡ ልቤ ፡ ቢሆንልኝ ፡ ኦሆሆ
በቅኔ ፡ ተሞልቶ ፡ አሃሃ ፡ ፊትህ ፡ ቢፈስልኝ ፡ ኦሆሆ
አንተ ፡ ካደረግኸኝ ፡ አሃሃ ፡ የአንተ ፡ የክብር ፡ እቃ ፡ አሃሃ
ኢየሱሴ ፡ ተመስገን ፡ ኦሆሆ ፡ ምሥጋናዬን ፡ እንካ ፡ አሃሃ

አዝ፦ ካረካህ ፡ ከወደድከው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ካስደሰተህ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ በየዕለቱ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ
ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ በየዕለቱ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ

ምህረትና ፡ ፀጋ ፡ አሃሃ ፡ ፍቅር ፡ የበዛለት ፡ ኦሆሆ
ኧረ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ አሃሃ ፡ መልካም ፡ ያደረግህለት ፡ ኦሆሆ
አንተ ፡ ደስ ፡ ካለህ ፡ አሃሃ ፡ ካረካህ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ኤሄሄ
እገዛልሃለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታዬ ፡ በሁለንተናዬ ፡ ኤሄሄ

አዝ፦ ካረካህ ፡ ከወደድከው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ካስደሰተህ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ በየዕለቱ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ
ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ በየዕለቱ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ

መቅደስህ ፡ ባለበት ፡ አሃሃ ፡ ክብርህ ፡ በሞላበት ፡ ኦሆሆ
እንዴት ፡ ደስ ፡ ያሰኛል ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለሥምህ ፡ መቀኘት ፡ ኦሆሆ
ስምህ ፡ ሞገሴ ፡ ነው ፡ አሃሃ ፡ መገኘትህ ፡ ፈውሴ ፡ ኤሄሄ
አክብሮትን ፡ ታብዛ ፡ አሃሃ ፡ ታመስግንህ ፡ ነብሴ ፡ ኤሄሄ

አዝ፦ ካረካህ ፡ ከወደድከው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ካስደሰተህ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ በየዕለቱ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ
ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ በየዕለቱ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ