Daniel Amdemichael/Yehonal/Ejeg Yakoragnal

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል
ርዕስ እጅግ ያኮራኛል
አልበም ይሆናል

አዝ
እጅግ ያኮራኛል ጌታ የአንተ መሆኔ
አተረፍኩኝ እንጂ አልከሰርኩም እኔ
አጋጣሚ አይደለም ኢየሱስ የአንተ እቅድ ነው
ወደ ፍቅርህ መንግሥት እንድፈልስ ያደረገው

ክብርህን ላውራው ልናገረው
በሰጠኸኝ ዜማ
ሁሉ በአንተ የሆነልኝን ላሰማ ምሥጋና
ኩራት ኩራት ኩራት አለኝ ፍቅርህን ሳስበው
ለአንተ መለየቴ ጌታ ለእኔ ክብሬ ይኼው ነው።

ፍቅርህ ከሁሉም በላይ በልጦብኛል
እንዳመልክህ ሁል ጊዜ ግድ ይለኛል
እንዴት ብዬ የሆዴን ልናገረው
ተመስገን ከማለት ሌላ ቃላት አጣሁ

እንዴት ብዬ የሆዴኑ ልናገረው
ምሥጋናዬ ምስጋና ማደሪያህን ይሙላው
እንዴት ብዬ የሆዴኑ ልናገረው
ምሥጋናዬ ምሥጋና ማደሪያህን ይሙላው

አዝ
እጅግ ያኮራኛል ጌታ የአንተ መሆኔ
አተረፍኩኝ እንጂ አልከሰርኩም እኔ
አጋጣሚ አይደለም ኢየሱስ የአንተ እቅድ ነው
ወደ ፍቅርህ መንግሥት እንድፈልስ ያደረገው

ክብርህን ላውራው ልናገረው
በሰጠኸኝ ዜማ ሁሉ በአንተ የሆነልኝን ላሰማ ምሥጋና
ኩራት ኩራት ኩራት አለኝ ፍቅርህን ሳስበው
ለአንተ መለየቴ ጌታ ለእኔ ክብሬ ይኼው ነው

ዛሬማ ሰው አድርጐኛል ድንቅ ፍቅርህ
ሞገስ ሆኖኛል ጌታ ክቡር ሥምህ
በውዳሴ የተሞላ በምሥጋና
መዝሙር ይዘመርልህ የአንተ ነውና
በፈቃዴ ውዳሴን እጨምራለሁ
መድሃኒቴ ጌታ ነህ አነግስሃለሁ (፪x)

አዝ
እጅግ ያኮራኛል ጌታ የአንተ መሆኔ
አተረፍኩኝ እንጂ አልከሰርኩም እኔ
አጋጣሚ አይደለም ኢየሱስ የአንተ እቅድ ነው
ወደ ፍቅርህ መንግሥት እንድፈልስ ያደረገው
ክብርህን ላውራው ልናገረው
በሰጠኸኝ ዜማ

ሁሉ በአንተ የሆነልኝን ላሰማ ምሥጋና
ኩራት ኩራት ኩራት አለኝ ፍቅርህን ሳስበው
ለአንተ መለየቴ ጌታ ለእኔ ክብሬ ይኼው ነው

ሁሉ በአንተ የሆነ ያማረለት
ከአምላኩ ጋር መንገዱ የቀናለት
ኤረ እንደ እኔ ማን አለ ቸር ጌታዬ
ክቡር ሥምህን ልባርከው በዜማዬ

ክቡር ሥምህን አምላኬ ዛሬም ልባርከው
መድሃኒቴ ጌታ ነህ አነግስሃለሁ (፪)

አዝ
እጅግ ያኮራኛል ጌታ የአንተ መሆኔ
አተረፍኩኝ እንጂ አልከሰርኩም እኔ
አጋጣሚ አይደለም ኢየሱስ የአንተ እቅድ ነው
ወደ ፍቅርህ መንግሥት እንድፈልስ ያደረገው

ክብርህን ላውራው ልናገረው
በሰጠኸኝ ዜማ ሁሉ በአንተ የሆነልኝ ላሰማ ምሥጋና
ኩራት ኩራት ኩራት አለኝ ፍቅርህን ሳስበው
ለአንተ መለየቴ ጌታ ለእኔ ክብሬ ይኸው ነው