Daniel Amdemichael/Yehonal/Destayie
- አዝ፦ ደስታዬ ፡ በጌታ ፡ ሙሉ ፡ ነው ፡ ከእንግዲህ ፡ ምንስ ፡ ያሻኛል
- ምድር ፡ ከሚታየው ፡ ሃብት ፡ ይልቅ ፡ የአምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ማርኮኛል
- የምድር ፡ ዝና ፡ ከበሬታ ፡ ሃላፊ ፡ ነው ፡ ትቼዋለሁ
- የአምላኬ ፡ ክብር ፡ ባለበት ፡ የእኔስ ፡ ሃገር ፡ በሠማይ ፡ ነው
- ኦ ፡ ቃሉ ፡ እንደሚናገረው ፡ ሃሌሉያ
እኔስ ፡ በአደባባዮቹ ፡ መዋል ፡ ማደር ፡ ይሻለኛል የአምላኬ ፡ ክብር ፡ ሲገለጥ ፡ ውስጤን ፡ ልቤን ፡ ያረካኛል የኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ ዘወትር ፡ አይለወጥም በቸርነቱ ፡ ይዞኛል ፡ ከቤቱ ፡ የትም ፡ አልሄድም
- አዝ፦ ደስታዬ ፡ በጌታ ፡ ሙሉ ፡ ነው ፡ ከእንግዲህ ፡ ምንስ ፡ ያሻኛል
- ምድር ፡ ከሚታየው ፡ ሃብት ፡ ይልቅ ፡ የአምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ማርኮኛል
- የምድር ፡ ዝና ፡ ከበሬታ ፡ ሃላፊ ፡ ነው ፡ ትቼዋለሁ
- የአምላኬ ፡ ክብር ፡ ባለበት ፡ የእኔስ ፡ ሃገር ፡ በሠማይ ፡ ነው
- ኦ ፡ ቃሉ ፡ እንደሚናገረው ፡ ሃሌሉያ
ለእኔስ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ ፡ የዘለዓለም ፡ መኖሪያዬ ክብሩን ፡ አይቼ ፡ እጠግባለሁ ፡ ሞገስ ፡ ፈሷል ፡ በላዬ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መሆን ፡ እመርጣለሁ ፡ የእርሱ ፡ ክብር ፡ በሞላበት መኖሪያዬን ፡ አድርጐታል ፡ እግዚአብሔር ፡ በሚገኝበት