Daniel Amdemichael/Yehonal/Alamarerewem

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል ርዕስ አላማርረውም አልበም ይሆናል

አዝ ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ባይሞላ በዚህ አልመዝነውም ከሁኔታዎች በላይ ነው ማንም አይከሰውም (፪x)

አቤት የእኔ ጌታ አሰራሩ ግሩም የዘገየ ሲመስል ማንም አይቀድመውም ቢሆንም ባይሆንም ለእኔ ፀጋው ይበቃኛል ቢሆንም ባይሆንም ለእኔ ፍቅሩ ይበቃኛል

አዝ ነገር ቢሞላ ባይሞላ በዚህ አልመዝነውም ከሁኔታዎች በላይ ነው ማንም አይከሰውም (፪x)

ሁልጊዜ መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ እግሬን በቤቱ ለእኔስ ፍቅሩ ይበቃኛል እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል እርሱ ነው የእኔ እድል ፈንታ እርስቴ የሕይወቴ መከታ ሁልጊዜ በእርሱ ደስ ይለኛል ከሁሉ ፍቅሩ በልጦብኛል

አዝ ነገር ቢሞላ ባይሞላ በዚህ አልመዝነውም ከሁኔታዎች በላይ ነው ማንም አይከሰውም (፪x)

አቤት የእኔ ጌታ አሰራሩ ግሩም የዘገየ ሲመስል ማንም አይቀድመውም ቢሆንም ባይሆንም ለእኔ ፀጋው ይበቃኛል ቢሆንም ባይሆንም ለእኔ ፍቅሩ ይበቃኛል

የሰው ፍላጐቱ ብዙ ነው የእግዚአብሔርን ፍቃድ እስኪለየው በልቤ ብዙ ሃሳብ ይኖራል የእግዚአብሔር የሆነው ይፀናል ይፀናልኝ ለእኔስ የእርሱ ሃሳብ ፈቃዱን ለመጣስ አልሻም ሃሳቤን የእርሱ ሃሳብ ይወረሰው ሲገለጥ ሁሉም ለበጐ ነው

ተግቶ ለጠበቀው ጌታ ሲሰጥ ምላሹን ለምን ተስፋ ልቁረጥ ሳልዘልቅ በትንሹ መታገስ ጥሩ ነው ብዙ ድንቅን ያሳያል ፀንቶ የጠበቀ መልካም ፍሬ ይበላል ከሁሉ የበለጠ ክብሩን አይቻለሁ ወደር የለሽ ፍቅሩን ምሕረት አግኝቻለሁ በትልቅ ትንሹ እንዴት አማርራለሁ የተደረገልኝ እጅግ እጅግ ብዙ ነው።