የተመሰገነ (Yetemesegene) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 5.png


(5)

ሰላም
(Selam)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2008)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

አዝ:- በሰማይ ፡ በምድር ፡ የተመሰገነ
በስራው ፡ ጻድቅ ፡ ነው ፡ እጅግ ፡ የታመነ
ሰማይን ፡ በኃይሉ ፡ በቃሉ ፡ ያጸና
እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ ገናና
ኦሆ ፡ ገናና ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ገናና ፡ ነው
ኦሆ ፡ ገናና ፡ ነው (፪x)
የእኛ ፡ ጌታ ፡ ታላቅ ፡ ገናና ፡ ነው

እናንተ ፡ መኳንንቶች ፡ በሮችን ፡ ክፈቱ
ንጉሡን ፡ ንጉሡን ፡ አስገቡ
ይህ ፡ የክብር ፡ ንጉሥ ፡ ግርማው ፡ የሚያስፈራ
በኃይሉ ፡ ተዐምር ፡ የሚሰራ
ሃያል ፡ ሃያል ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ሃያል (፫x)
ሃያል ፡ ሃያል ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ሃያል

አዝ:- በሰማይ ፡ በምድር ፡ የተመሰገነ
በስራው ፡ ጻድቅ ፡ ነው ፡ እጅግ ፡ የታመነ
ሰማይን ፡ በኃይሉ ፡ በቃሉ ፡ ያጸና
እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ ገናና
ኦሆ ፡ ገናና ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ገናና ፡ ነው
ኦሆ ፡ ገናና ፡ ነው (፪x)
የእኛ ፡ ጌታ ፡ ታላቅ ፡ ገናና ፡ ነው

እግዚአብሔር ፡ ብርቱ ፡ በሰልፍም ፡ ሃይለኛ
ተዋጊ ፡ ለተጠቃው ፡ ዳኛ
የዙፋኑ ፡ መሰረት ፡ ጽድቅና ፡ እውነት ፡ ነው
እልልታ ፡ ክብር ፡ ለሚገባው
ሰማይ ፡ ዙፋኑ ፡ ነው ፡ ምድር ፡ የእግሩ ፡ መርገጫ
በታሪክ ፡ ነው ፡ የሌለው ፡ አቻ
እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ በማን ፡ ይመሰላል
በግርማው ፡ ፍጥረት ፡ ይደነቃል
ሃያል ፡ ሃያል ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ሃያል
ሃያል ፡ ሃያል ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ሃያል (፪x)

አዝ: በሰማይ ፡ በምድር ፡ የተመሰገነ
በስራው ፡ ጻድቅ ፡ ነው ፡ እጅግ ፡ የታመነ
ሰማይን ፡ በኃይሉ ፡ በቃሉ ፡ ያጸና
እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ ገናና
ኦሆ ፡ ገናና ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ገናና ፡ ነው
ኦሆ ፡ ገናና ፡ ነው (፪x)
የእኛ ፡ ጌታ ፡ ታላቅ ፡ ገናና ፡ ነው
ኦሆ ፡ ገናና ፡ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ገናና ፡ ነው
ኦሆ ፡ ገናና ፡ ነው (፪x)
የእኛ ፡ ጌታ ፡ ታላቅ ፡ ገናና ፡ ነው