From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ:- በቀንም ፡ በሌሊት ፡ ጌታዬ ፡ ይጠብቀኛል
አሃአሃ ፡ ይጠብቀኛል ፡ እህእህ
እንደ ፡ አምላኬ ፡ ያለ ፡ ከወዴት ፡ ይገኛል
አሃአሃ ፡ ከየት ፡ ይገኛል ፡ ሆሆሆ ፡ ከየት ፡ ይገኛል
መውጣቴ ፡ መግባቴ ፡ ከእርሱ ፡ ተጠብቆ
ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ተተንቅቆ
በምህረቱ ፡ ታድጓታል ፡ ነፍሴን ፡ ከእሳት ፡ ነጥቆ
የእርሱን ፡ ደግነት ፡ ለሰው ፡ እነግራለው
አያሳፍርም ፡ ሁሌ ፡ ታማኝ ፡ ነው
በሥም ፡ የሚያውቀኝ ፡ የሆነኝ ፡ ጥላ
ኢየሱስ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ከለላ
አዝ:- በቀንም ፡ በሌሊት ፡ ጌታዬ ፡ ይጠብቀኛል
አሃአሃ ፡ ይጠብቀኛል ፡ እህእህ
እንደ ፡ አምላኬ ፡ ያለ ፡ ከወዴት ፡ ይገኛል
አሃአሃ ፡ ከየት ፡ ይገኛል ፡ ሆሆሆ ፡ ከየት ፡ ይገኛል
ትንፋሼን ፡ መንገዴን ፡ በእጁ ፡ ለያዘው
የሰማዩን ፡ ፍቅር ፡ ሰላም ፡ ውስጤ ፡ ላፈሰሰው
በማዳኑ ፡ ደስ ፡ እያለኝ ፡ አመሰግናለሁ
ታሪክም ፡ የለኝ ፡ ታሪኬ ፡ እርሱ ፡ ነው
ከልጅነቴ ፡ እጄን ፡ የያዘው
ምስክሩ ፡ ነኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ይንገሥ
መልካም ፡ እረኛ ፡ ስሙ ፡ ኢየሱስ
አዝ:- በቀንም ፡ በሌሊት ፡ ጌታዬ ፡ ይጠብቀኛል
አሃአሃ ፡ ይጠብቀኛል ፡ እህእህ
እንደ ፡ አምላኬ ፡ ያለ ፡ ከወዴት ፡ ይገኛል
አሃአሃ ፡ ከየት ፡ ይገኛል ፡ ሆሆሆ ፡ ከየት ፡ ይገኛል
|