From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ያ ፡ የጥንቱ ፡ ፍቅራችን ፡ መሃላችን ፡ የታለ
ኀጢአታችን ፡ በዝቶ ፡ ጥላቻን ፡ አበቀለ
ከአንተ ፡ ያልተቀበልነው ፡ ያልሰጠኸን ፡ ምን ፡ አለ
ሁሉም ፡ ተረስቶ ፡ ዛሬ ፡ ትዕቢታችን ፡ ከፍ ፡ አለ
አዝ:- ኢየሱስ (፪x) ፡ በማስተዋል ፡ ሙላን ፡ በማስተዋል (፪x)
ኀጢአት ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ አይሆንም ፡ ልማት
ሞትን ፡ ይወልዳል ፡ ለሕይወት ፡ ጥፋት
ደሙ ፡ ያላጠበው ፡ ያልተመለሰ
እናስብ ፡ እንጂ ፡ ከየት ፡ ደረሰ
ምክንያት ፡ አንደርድር ፡ ለድካማችን
ከሞት ፡ ያድናል ፡ መመለሳችን
ኑሯችን ፡ ከንቱ ፡ ከእውነት ፡ የሚጣረስ
ንሰሃ ፡ እንግባ ፡ ሳናለባብስ
ቦታ ፡ አጥቶ ፡ ቅድስና ፡ ኀጢአት ፡ ተሞልቷል ፡ ቤቱ
ሁሉም ፡ አንተን ፡ አልፈራም ፡ ይስታል ፡ በአንደበቱ
የጥበብ ፡ መጀመሪያው ፡ አንተን ፡ መፍራቱ ፡ ጠፍቶ
ሁሉ ፡ እንዳሻው ፡ ይሄዳል ፡ ቤቱ ፡ በአመጽ ፡ ተሞልቶ
አዝ:- ኢየሱስ (፪x) ፡ በማስተዋል ፡ ሙላን ፡ በማስተዋል (፪x)
ከየት ፡ ተማርነው ፡ ወንድምን ፡ መጥላት
ከነብያት ፡ ነው ፡ ወይንስ ፡ ከሓዋርያት
የቀደሙትን ፡ የምናውቃቸው ፡ በመልካም ፡ ፍቅር ፡ በጸሎታቸው
ለእውነት ፡ እንኑር ፡ ከቶ ፡ አንገበዝ
ደሙ ፡ ያነጻናል ፡ ቶሎ ፡ እንመለስ
የሰማይ ፡ ጥበብ ፡ የላይኛይቱን
ከአምላክ ፡ እንለምን ፡ ይሰማል ፡ ሁሉን (፪x)
|