Daniel Amdemichael/Selam/Ersu New

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ርዕስ እርሱ ነው ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል አልበም ሰላም

አዝ እርሱ ነው የደሃ ደግ ወዳጅ የባልቴቶች ዳኛ ድሃውን ምግቡን የሚያጐርሰው ጾሙን እንዳይተኛ የተጣለውን አይቶ የማያልፍ ከትቢያ ሚያነሳው እሩህሩህ ነው ጌታ

ወዳጅ ዘመድ ገፍቶ ላራቀው ኢየሱስ ይደርስለታል አምላኬ ይደርስለታል ልቡን ሃዘን በጣም ለጐዳው መጽናናት ይሆንለታል (፪x) ማረፊያ ነው ለተጣለው ሰው አይተናል እንባውን ሲያብሰው (፪x) ከቅዱሳን መሃል ሲያቆመው ሲያከብረው ሞገስ ሲሆነው (፪x)

ድንቅ ፍቅሩን አይቻለሁ መጠጊያ ሆኖኝ መድህኔ ወጀቡ እንዳያንገላታኝ ኢየሱስ ሲቆም ከጐኔ ባወራው ቃላት ያጥረኛል ብቆጥረው የእርሱን ውለታ እንዲያው ላመስግነው እንጂ በጠዋት ደግሞም በማታ

አዝ እርሱ ነው የደሃ ደግ ወዳጅ የባልቴቶች ዳኛ ድሃውን ምግቡን የሚያጐርሰው ጾሙን እንዳይተኛ የተጣለውን አይቶ የማያልፍ ከትቢያ ሚያነሳው እሩህሩህ ነው ጌታ

ቸርነቱን ያውራ የቀመሰው ይዘምር እንደኔ ያለው (፪x) ማቁን ቀዶ ደስታ ያስታጠቀው ምህረቱ ሰው ያደረገው (፪x) ምንም የለም የኔ የምለው አንድ ሁለት ብዬ ምቆጥረው (፪x) ጽድቄም ቅድሳዬ እርሱ ነው በመስቀል ለእኔ የሞተው በመስቀል ሁሉን የሰራው

ሁሉም ነገር ተፈጸመ ተፈጸመ ያለ ለታ አሮጌው ማንነት አልፎ በአዲሱ ሕይወት ተተካ አፋቸው ምሥጋና ሰማ ኢሄ ሚስጥር የገባቸው በትንሳኤው የለበሱት ኢየሱስ ሁኖ ኑሯቸው

ለእኔስ ብርሃን በርታልኛለች ከሰማይ ድምቅ እያለች (፪x) ጨለማውን እየገፈፈች የጌታን ጽድቅ እያሳየች የአምላኬን ጽድቅ እያሳየች የመስቀሉ ስራ ስገለጥ በሕይወቴ እውነት ሲበራ አስታረቀኝ ከአምላኬ ጋራ ይዘመር ይሄስ ይወራ (፪x) ምሰጠው አንዳች የእልኝም ማን ልበለው መድሃኒቴን ምሥጋናን ሰላም ደስታን እርካታን ሞልቷል ሕይወቴን ልቀኝለት አዲስ ቅኔን ይበልጣል እርሱ የፈቀደው ለሥሙ ምሥጋና ይሁን ለኢየሱስ ጌታ ለሆነው

አዝ እርሱ ነው የደሃ ደግ ወዳጅ የባልቴቶች ዳኛ ድሃውን ምግቡን የሚያጐርሰው ጾሙን እንዳይተኛ የተጣለውን አይቶ የማያልፍ ከትቢያ ሚያነሳው እሩህሩህ ነው ጌታ።