From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ:- አሁንማ ፤ ብርሃንህ ፡ በእኔ ፡ ደምቋል
መከራም ፡ ከኔ ፡ ርቋል ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ምን ፡ እላለሁ ፤ ስምክን ፡ ከማክበር ፡ በቀር ፡
ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር ፡ ስላደረክልኝ ፡ ነገር (፪x)
በዓለም ፡ ላይ ፡ ከሚታየው ፡ ከአልማዝ ፡ ከወርቅ ፡ ከዕንቁ
የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ይበልጣል ፡ አባት ፡ ነህ ፡ ለተጠቁ
ምስክር ፡ ነኝ ፡ ለዚህ ፡ እኔ ፡ ማዳንህን ፡ አይቻለሁ
ያባትነት ፡ ፍቅርህን ፡ ምህረትህን ፡ እዘምራለሁ
ተመስገን ፡ እያልኩ ፡ ላክብር ፡ ስምህን
በእርግጥ ፡ ስላየሁ ፡ ጌትነትህን
በአማረ ፡ ዜማ ፡ ቅኔ ፡ ውዳሴ
ልዑል ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ያክብርህ ፡ ነፍሴ
አዝ:- አሁንማ ፤ ብርሃንህ ፡ በእኔ ፡ ደምቋል
መከራም ፡ ከኔ ፡ ርቋል ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ምን ፡ እላለሁ ፤ ስምክን ፡ ከማክበር ፡ በቀር ፡
ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር ፡ ስላደረክልኝ ፡ ነገር (፪x)
ማረፊያ ፡ ለምስኪኑ ፡ ማጠጊያ ፡ ለደሃው ፡ ሰው
ይህንን ፡ አይቻለሁ ፡ እንባውን ፡ ስታብሰው
ደግ ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ግሩም ፡ በምክርህ
ምህረትህ ፡ አይለካም ፡ ወደር ፡ የለው ፡ ለፍቅርህ
አሉ ፡ ብዙዎች ፡ የታደጋቸው
ስምህን ፡ የሚጠሩ ፡ በምሥጋናቸው
እያደነቁ ፡ ግሩም ፡ ስምህን
ይዘምራሉ ፡ ጌትነትህን
አዝ:- አሁንማ ፤ ብርሃንህ ፡ በእኔ ፡ ደምቋል
መከራም ፡ ከኔ ፡ ርቋል ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ምን ፡ እላለሁ ፤ ስምክን ፡ ከማክበር ፡ በቀር ፡
ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር ፡ ስላደረክልኝ ፡ ነገር (፪x)
|