Daniel Amdemichael/Selam/Amlakie Feqrehen
አምላኬ ፍቅርህን ልንገር ምሥጋናህን (፪x)
እንከን የሌለብህ አባት መሆንህን (፪x)
በደምህ ቀድሰህ ያለበስከኝ ጸጋህ(፪x)
ሁሌ ያዘምረኛል አኑሮኝ ከአንተ ጋር (፪x)
በስምህ አምኜ ልጅህ በመሆኔ
ሁልጊዜ ተመስገን እላለሁኝ እኔ(፪x)
በዜማ በቅኔ ስምክን አውጃለሁ
ብዬ እየዘመርኩኝ ኢየሱስ ጌታ ነው (፪x)
ገብተህ ከመንደሬ ከተደበቅኩበት
ፍቅርህ ልቤን ገዛው እጄን የያዝክበት
የሕይወትን ትርጉም የመኖርን ሚስጥር
ገልጠህ አሳየኸኝ በመስቀልህ ፍቅር
ምህረትህን አሳየኸኝ አሳየኸኝ ይቅርታ
ሰላምን ሰጥተኸኛል አቻ የለህ ኢየሱስ የኔ ጌታ
ልዘምር በደስታ ከእንግዲህ ምን እላለሁ
እግዚአብሔር ከወደደኝ ዝቅ ብዬ አመሰግናለሁ
የትንሳዔው ንጉሥ የትንሳዔው ጌታ
ኢየሱስ የኔ ወዳጅ የሕይወቴ አለኝታ
የሕይወት ውኃ ነህ ጥሜን አርክተሃል
በረሃው ሕይወቴን አለምልመኸዋል
ደህንነት አግኝቻለሁ ዕዳዬ ተሰርዟል
ኩነኔ በእኔ የለም አቤት ፍቅርህ ይህንን አድርጓል
ክብር ለስምህ ይሁን ተትረፍርፏል ሰላሜ
በደስታ ላምልክህ ላመስግንህ ደግሜ ደግሜ
አዝ
ዛሬ ሰው መሆኔን ሳስብ ይገርመኛል
በደምህ ቀድሰህ የአንተ አድርገኸኛል
መዳኔስ ብቻውን ተዐምር አይደለም ወይ
በአንተ መመረጤስ ብርሃንን እንዳይ (፪)
ለአምልክህ ተሰጥቼ በሙሉ ልቤ ልቀኝ
ቃልህን ላሰላስለው በእውነት ልኑር አንተ እንዳስተማርከኝ
ቅንነት ልቤን ይውረስ ልኑር እንደምትወደው
አምልኮዬ ንጹህ ይሁን ምሥጋናዬም አንተ እምታሸተው