የተገለጠው ፡ እውነት (Yetegeletew Ewnet) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 3.png


(3)

ሞኝነት ፡ ሆኖ ፡ አይደለም
(Mognenet Hono Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፪ (1999)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

አዝ፦ አንደበትህ ፡ ዝም ፡ አይበል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል
የተገለጠው ፡ እውነት ፡ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል
ክንፍ ፡ አውጥቼ ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ እንድወጣ ፡ አድርጐኛል
የደከመ ፡ ጉልበቴን ፡ ጌታ ፡ አድሶልኛል

ጌታ ፡ ነዉ (፪x)
ጌታ ፡ ነዉ ፡ ኢየሱሴ ፡ ጌታ ፡ ነዉ
ኃያል ፡ ነዉ (፪x)
ኃያል ፡ ነዉ ፡ ጌታዬ ፡ ኃያል ፡ ነዉ

ፍቅሩ ፡ ተገልጧል ፡ ደግነቱ
ተስፋ ፡ ለቆረጡ ፡ ማጽናናቱ
አቤት ፡ ምሕረቱ (፬x)

ምህረቱ ፡ አጽንቶ ፡ አቁሞኛል
በኢየሱሴ ፡ ብርሃን ፡ ወጥቶልኛል
ዘምራለሁ ፡ ንጉሤን ፡ አከብራለሁ
የእርሱን ፡ ማዳን ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ አወራለሁ

አዝ፦ አንደበትህ ፡ ዝም ፡ አይበል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል
የተገለጠው ፡ እውነት ፡ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል
ክንፍ ፡ አውጥቼ ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ እንድወጣ ፡ አድርጐኛል
የደከመ ፡ ጉልበቴን ፡ ጌታ ፡ አድሶልኛል

ጌታ ፡ ነዉ (፪x)
ጌታ ፡ ነዉ ፡ ኢየሱሴ ፡ ጌታ ፡ ነዉ
ኃያል ፡ ነዉ (፪x)
ኃያል ፡ ነዉ ፡ ጌታዬ ፡ ኃያል ፡ ነዉ

አፌን ፡ በዝማሬ ፡ እከፍታለሁ
የጌታዬን ፡ ክብር ፡ አወራለሁ
ንጉሥ ፡ እለዋለሁ (፬x)

እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ዘለዓለም ፡ ድንቅ ፡ ጌታ
ይገባዋል ፡ ምሥጋና ፡ በዕልልታ
ኦ! አክብሪው ፡ ነፍሴ ፡ ለእርሱ ፡ ተገዢ
ዛሬም ፡ ነገም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ተስፋሽ

አዝ፦ አንደበትህ ፡ ዝም ፡ አይበል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል
የተገለጠው ፡ እውነት ፡ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል
ክንፍ ፡ አውጥቼ ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ እንድወጣ ፡ አድርጐኛል
የደከመ ፡ ጉልበቴን ፡ ጌታ ፡ አድሶልኛል

ጌታ ፡ ነዉ (፪x)
ጌታ ፡ ነዉ ፡ ኢየሱሴ ፡ ጌታ ፡ ነዉ
ኃያል ፡ ነዉ (፪x)
ኃያል ፡ ነዉ ፡ ጌታዬ ፡ ኃያል ፡ ነዉ

ዝማሬ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ኦ! ምሥጋና
ደግሜ ፡ ልባርከው ፡ ቸር ፡ ነውና
ዛሬም ፡ እንደገና (፬x)

ኦ! ጌታዬን ፡ ሁልጊዜ ፡ አመልከዋለሁ
ዘወትር ፡ ፊቱ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ
አልሰለችም ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ብርታትና ፡ ኃይል ፡ ሆኖኛል

አዝ፦ አንደበትህ ፡ ዝም ፡ አይበል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል
የተገለጠው ፡ እውነት ፡ መቼ ፡ ዝም ፡ ያሰኛል
ክንፍ ፡ አውጥቼ ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ እንድወጣ ፡ አድርጐኛል
የደከመ ፡ ጉልበቴን ፡ ጌታ ፡ አድሶልኛል

ጌታ ፡ ነዉ (፪x)
ጌታ ፡ ነዉ ፡ ኢየሱሴ ፡ ጌታ ፡ ነዉ
ኃያል ፡ ነዉ (፪x)
ኃያል ፡ ነዉ ፡ ጌታዬ ፡ ኃያል ፡ ነዉ