የልብ ፡ ወዳጅ (Yeleb Wedaj) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 3.png


(3)

ሞኝነት ፡ ሆኖ ፡ አይደለም
(Mognenet Hono Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፪ (1999)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

አዝ፦ ከእናቴም ፡ ከአባቴም ፡ ይልቅ ፡ የሚጠጋጋኝ ፡ ዘመዴ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መከታ ፡ ለእኔ ፡ አፍቃሪ ፡ የልብ ፡ ወዳጄ (፪x)

ፍቅሩን ፡ ሳስብ ፡ ይደንቀኛል ፡ ለእኔ ፡ ያሳየው ፡ ምህረቱ
ባወራው ፡ ባወራው ፡ አያልቅ ፡ ችሎኝ ፡ አለሁ ፡ በቤቱ
ትዕግሥቱ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አይሰለችም ፡ ይሸከማል
መልካም ፡ የበጐች ፡ እረኛ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ከየት ፡ ይገኛል

አዝ፦ ከእናቴም ፡ ከአባቴም ፡ ይልቅ ፡ የሚጠጋጋኝ ፡ ዘመዴ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መከታ ፡ ለእኔ ፡ አፍቃሪ ፡ የልብ ፡ ወዳጄ (፪x)

ውድ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ጌታዬ ፡ ዕንቁና ፡ ወርቅን ፡ ያስንቃል
ጠረኑ ፡ ከሩቅ ፡ የሚስብ ፡ መዓዛውም ፡ ደስ ፡ ያሰኛል
ፍቅር ፡ አለው ፡ ልብ ፡ የሚያረካ ፡ ወዳጄ ፡ ወረት ፡ አያውቅም
ነፍሱን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ለውጧል ፡ ፍቅሩን ፡ በሞት ፡ ገልጾልኛል

አዝ፦ ከእናቴም ፡ ከአባቴም ፡ ይልቅ ፡ የሚጠጋጋኝ ፡ ዘመዴ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መከታ ፡ ለእኔ ፡ አፍቃሪ ፡ የልብ ፡ ወዳጄ (፪x)

ታማኝ ፡ ነው ፡ የማይለወጥ ፡ ጓደኛ ፡ ጊዜ ፡ አይቶ ፡ የማይርቅ
የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ዋሴ ፡ ኢየሱስ ፡ አዳኝ ፡ ለነፍሴ
ድቅድቅ ፡ ጨለማን ፡ የሚገፍ ፡ ብርሃን ፡ ይሁን ፡ ይብራ ፡ ያለ
ድንቁ ፡ የሰላም ፡ አለቃ ፡ ኧረ ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ አለ

አዝ፦ ከእናቴም ፡ ከአባቴም ፡ ይልቅ ፡ የሚጠጋጋኝ ፡ ዘመዴ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መከታ ፡ ለእኔ ፡ አፍቃሪ ፡ የልብ ፡ ወዳጄ (፪x)