ሰላም (Selam) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 3.png


(3)

ሞኝነት ፡ ሆኖ ፡ አይደለም
(Mognenet Hono Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፪ (1999)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:01
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

በአምሳልህ ፡ የተሠራ ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ክቡር ፡ ነው
መራብ ፡ መሰደዱ ፡ መሞቱ ፡ ለምን ፡ ነው?
ምድራችንን ፡ ማራት ፡ እባክህ ፡ አምላካችን
ንስሃ ፡ እንገባለን ፡ በፊትህ ፡ ሁላችን

አዝሰላም (፬x) ፡ ለምድራችን

ስለ ፡ አባቶች ፡ በደል ፡ ማረን ፡ እንላለን
ስለ ፡ ልጆች ፡ በደል ፡ ማረን ፡ እንላለን
ጦርነት ፡ ከምድር ፡ ጩኸት ፡ ዋይታው ፡ ይብቃ
ጨለማችን ፡ በርቶ ፡ በሰላም ፡ ይተካ

አዝሰላም (፬x) ፡ ለምድራችን (፪x)

የሰላሙን ፡ አየር ፡ ሁሉም ፡ ተጠምቶታል
ጦርነት ፡ ስደትን ፡ ጆሮው ፡ ሰልችቶታል
የሰላም ፡ አለቃ ፡ ሁሉም ፡ በእጅህ ፡ ነው
ምድራችንን ፡ ማራት ፡ ሰላሟ ፡ በአንተ ፡ ነው

አዝሰላም (፬x) ፡ ለምድራችን

ትምክህት ፡ እልሃችን ፡ ይራቅ ፡ ከእኛ ፡ ይጥፋ
ፍቅር ፡ መተሳሰብ ፡ በምድራችን ፡ ይስፋ
ጦርነትን ፡ ሻረው ፡ ቀስቱንም ፡ ስበረው
ሰላም ፡ ለሰው ፡ ልጆች ፡ ባይበሉም ፡ ጥጋብ ፡ ነው