From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል
ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል
ምሕረቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል
ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል
የድሃ ፡ አደግ ፡ ወዳጅ ፡ የምስኪን ፡ ጓደኛ
ማን ፡ እንደ ፡ ኢየሱሴ ፡ ታማኝ ፡ ሚስጥረኛ
መድኃኒቴ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ አመልከዋለሁ
ምሥጋናም ፡ ክብርም ዝማሬም ፡ ለእርሱ ፡ ነው (፮x)
አዝ፦ ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል
ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል
ምሕረቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል
ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል
ኃጥያተኛ ፡ ብሎ ፡ ሁሉም ፡ ተፀይፏት
ያለርህራሄ ፡ በድንጋይ ፡ ሊወግሯት
እንዳትሞት ፡ የሚፈልግ ፡ ተገኘ ፡ የሚወዳት
ጥበብን ፡ ተናግሮ ፡ ከጨካኙ ፡ አዳናት
አትሞቺም ፡ አላት(፭x)
አዝ፦ ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል
ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል
ምሕረቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል
ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል
የአንዲቷ ፡ ነፍስ ፡ ጌታን ፡ በጣም ፡ ግድ ፡ ብሎት
በሰማሪያ ፡ መንገድ ፡ አለፈ ፡ ሊያድናት
የነፍሷን ፡ ጥያቄ ፡ የውስጧን ፡ ፈታላት
የሕይወትን ፡ ውኃ ፡ አፍለቀለቀላት
አትጠሚም ፡ አላት(፭x)
አዝ፦ ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል
ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል
ምሕረቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል
ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል
አቤቱ ፡ ጌታዬ ፡ ሁሌ ፡ አከብርሃለሁ
ፍቅርህን ፡ እያሰብኩ ፡ እገዛልሃለሁ
ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ንገሥ ፡ ለዘለዓለም
በሰማይ ፡ በምድር ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ የለም (፮x)
|