Daniel Amdemichael/Mognenet Hono Aydelem/Mognenet Hono Aydelem

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል

ርዕስ ሞኝነት ሆኖ አይደለም

አዝ

ሞኝነት ሆኖ አይደለም ፍቅሩን ቀምሼ ነው

ና ሲለኝ የተከተልኩት ነፍሴ ተማርካ ነው

ጠቢባን ያላዩት ዕውቀት ለእኔ ተገልጦ ነው

የጌታን የማዳን ሚስጢር ነፍሴ ተረድታው ነው


ከወርቅ ከዕንቁ በልጦብኝ ነው

ከማንም በላይ ተመችቶኝ ነው

የቱ ነው ታዲያ ሞኝነቱ

ለእኔ ጥበብ ነው ጌታን ማወቁ ኤሄሄ (፪x)

አምላኬን ማወቄ አምላኬን ማወቄ አሃሃ/ኦሆሆ አምላኬን ማወቄ (፪x)


እኔስ መድኃኒቴን ተስፋ አደርገዋለሁ

እኔስ ኢየሱሴን ተስፋ አደርገዋለሁ

ቢጐድልም ቢሞላው በእርሱ እታመናለሁ

እርሱ አይለየኝም ይህንን አውቃለሁ

ድንቁን አይቻለሁ በሕይወት ዘመኔ

ከኢየሱሴ በቀር ጌታ አላውቅም እኔ

ሞት ያላሸነፈው አምላክ እርሱ ብቻ

ዘመን የማይሽረው ነው የሌለው አቻ


አዝ

ምስክር ነኝ እኔ ኢየሱስ ያድናል

ከኃጢአት እሥራት ከደዌም ይፈታል

ሰላሙ ብዙ ነው እረፍትን ይሰጣል

ተስፋ ለቆረጡት ተስፋቸውን ያድሳል

ኃያላን ነን ያሉ በእርሱ ላይ ቢነሱ

ወድቀው ተረሱ እንጂ ለአፍታም አልታወሱ


የእኛ ግን ኢየሱስ በልባችን ያለው

ፍቅሩ የማይጠገብ ዘለዓለማዊ ነው


አዝ


ዓይኔ በርቶልኛል ጌታን አውቄያለሁ

ከዚህ በላይ የለም ምን እፈልጋለሁ

የዘለዓለም ሕይወት በነጻ አግኝቻለሁ

በእርሱ ተመርጬ በፊቱ አዜማለሁ

እዘምራለሁኝ አልታክትም ሁሌ

ስለ እርሱ ዝም ልል ከቶ አልችልም እኔ

የማዳኑን ወንጌል በዜማ አወራለሁ

ኢየሱስ ያድናል እመሰክራለሁ

አዝ