Daniel Amdemichael/Mognenet Hono Aydelem/Mech Eresahu

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ
መች እረሳሁ መች ዘነጋሁ ሁሉንም አስታውሳለሁ
ከሕጻንነቴ ጀምሮ ስትመራኝ ማዳንህን አይቻለሁ
እጆቼን ላንሳ ላክብርህ ምሥጋናዬን ተቀበለው
ብቻውን ተዓምር የሚያደርግ የሚሠራ
ኧረ እንዳንተ ያለ ማነው? /3/

የራራልኝ በድካሜ
ኃይል የሆነልኝ አቅሜ
ጐኔ ቆሞ ያበረታኝ
ማን ነበረ ከአንተ በላይ?

አዝ
መች እረሳሁ መች ዘነጋሁ

ከንፈሮቼን ቀባሃቸው
ጠላቶቼ እያየ ዓይናቸው
ዝማሬን በአፌ ጨምረሃል
አመልክህ ዘንድ ይገባኛል

አዝ
መች እረሳሁ መች ዘነጋሁ

ሁሉም አልፎ እዚህ መድረሴ
በአንተ እንጂ መች በራሴ
ክብር ለአንተ እሰጣለሁ
ሁልጊዜ እዘምራለሁ

አዝ መች እረሳሁ መች ዘነጋሁ