ሁሉን ፡ እንደዋዛ (Hulun Endewaza) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 3.png


(3)

ሞኝነት ፡ ሆኖ ፡ አይደለም
(Mognenet Hono Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፪ (1999)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:01
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

አዝ፦ ጌታ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ መልካም ፡ ያደረገው
እርሱ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው
አምላኬ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ ያደረገው
እርሱ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው
ይገርመኛል ፡ ይደንቀኛል
ኦ ፡ ጌታዬ ፡ ሥራው ፡ ይገርመኛል (፪x)

አምላኬ ፡ ባይርዳኝ ፡ እጄን ፡ ይዞ
እንዴት ፡ ይታለፋል ፡ ጠላቴ ፡ መንገድ ፡ ዘግቶ
ኦ ፡ ምሕረቱ ፡ ለእኔ ፡ ስለበዛ ፡ አሃ
አሳለፈኝ ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ እንደዋዛ (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ መልካም ፡ ያደረገው
እርሱ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው
አምላኬ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ ያደረገው
እርሱ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው
ይገርመኛል ፡ ይደንቀኛል
ኦ ፡ ጌታዬ ፡ ሥራው ፡ ይገርመኛል (፪x)

ዓይኖቼን ፡ ከፈተ ፡ ጌታ ፡ ገለጠልኝ
የሰማዩን ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ አበራልኝ
ኦ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በእርሱ ፡ ለዘለዓለም ፡ አሃ
አመልካለሁ ፡ ጌታን ፡ ኧረ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ የለም (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ መልካም ፡ ያደረገው
እርሱ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው
አምላኬ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ ያደረገው
እርሱ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው
ይገርመኛል ፡ ይደንቀኛል
ኦ ፡ ጌታዬ ፡ ሥራው ፡ ይገርመኛል (፪x)

በዕረፍት ፡ ውኃ ፡ ዘንድ ፡ እኔን ፡ የሚመራኝ
በጠላቶቼ ፡ ፊት ፡ ዘይትን ፡ የቀባኝ
ጽዋዬን ፡ ሞላው ፡ ጌታ ፡ አትረፈረፈኝ ፡ አሃ
በመንገዴ ፡ ላይ ፡ እርሱ ፡ ምርኩዜ ፡ ሆነልኝ (፪)

ሃሌሉ ፡ ሃሌሉያ (፫x)
ሃሌ ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ (፫x)

አዝ፦ ጌታ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ መልካም ፡ ያደረገው
እርሱ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው
አምላኬ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ ያደረገው
እርሱ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው