ፍቅሩን ፡ ቀምሼአለሁ (Feqrun Qemeshalehu) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 3.png


(3)

ሞኝነት ፡ ሆኖ ፡ አይደለም
(Mognenet Hono Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፪ (1999)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

አዝ፦ ፍቅሩን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ምሕረቱን ፡ አይቼዋለሁ
ድንቅ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ያረገዉ ፡ መድኃኒቴ
ኦ ፡ ኃያል ፡ ሥሙን ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው (፪x)

ምሕረቱን ፡ አይቻለሁ (፪x) ፡ ላመልከው ፡ ፈቅጃለሁ
ድንቅ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ (፪x) ፡ ያረገው ፡ መድኃኒቴ

ጉልበቴን ፡ አስገዛሁለት ፡ አምላኬን ፡ ሁሌ ፡ ላመልከው
በፍቅሩ ፡ ስቦ ፡ ማርኮኛል ፡ ምሕረቱም ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው
ስለዚህ ፡ ወደድኩት ፡ ለእርሱ ፡ ተገዛሁለት (፪x)

አዝ፦ ፍቅሩን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ምሕረቱን ፡ አይቼዋለሁ
ድንቅ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ያረገዉ ፡ መድኃኒቴ
ኦ ፡ ኃያል ፡ ሥሙን ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው

ምሕረቱን ፡ አይቻለሁ (፪x) ፡ ላመልከው ፡ ፈቅጃለሁ
ድንቅ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ (፪x) ፡ ያረገው ፡ መድኃኒቴ

ከእንግዲህ ፡ ፍቅሩ ፡ ማርኮኛል ፡ ሕይወቴን ፡ ሰጥቼዋለሁ
ሌላ ፡ ማንም ፡ አይገዛኝም ፡ ለኢየሱስ ፡ ተለይቻለሁ
በጣም ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ የአምላኬ/የጌታዬ ፡ ፍቅር ፡ ገዝቶኛል (፪x)

አዝ፦ ፍቅሩን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ምሕረቱን ፡ አይቼዋለሁ
ድንቅ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ያረገዉ ፡ መድኃኒቴ
ኦ ፡ ኃያል ፡ ሥሙን ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው

ምሕረቱን ፡ አይቻለሁ (፪x) ፡ ላመልከው ፡ ፈቅጃለሁ
ድንቅ ፡ ነው ፡ በሕይወቴ (፪x) ፡ ያረገው ፡ መድኃኒቴ

እኔስ ፡ ፍቅሩን ፡ አይቻለሁ ፡ በድካም ፡ ቢሆን ፡ በብርታት
ኢየሱስ ፡ ሁሌም ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ወዳጄ ፡ ወረት ፡ የለበት
ቃላቶች ፡ ያጥሩኛል ፡ ምን ፡ ብለው ፡ ያረካኛል (፪x)