እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለዋል (Ejeg Des Yelewal) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 3.png

(3)

ሞኝነት ፡ ሆኖ ፡ አይደለም
(Mognenet Hono Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፪ (1999)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

አዝ፦ አምላኬ/ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ በአንተ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ወደር ፡ የለው ፡ ምህረትህ ፡ ፊትህ ፡ አቁሞኛል
ሁልጊዜ ፡ ማለዳ ፡ አዲስ ፡ ነህ ፡ ፍቅርህ ፡ አቻ ፡ የሌለው
ቸርነትህ ፡ በዛልኝ ፡ ሥምህን ፡ ላመስግነው (፪x)

ምህረትህ ፡ አቁሞኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
በልቤ ፡ ላመስግንህ ፡ ፈቅጄም ፡ ልገዛልህ (፪x)

ያስፈነድቀኛል ፡ ምህረቱ ፡ በዝቶ
ዘምር ፡ ያሰኘኛል ፡ ቸርነቱ ፡ በዝቶ
አመስግነው ፡ ይለኛል ፡ ደስ ፡ ደስም ፡ ይለኛል
አመስግን ፡ ይለኛል ፡ አሃ ፡ አሃ (፪x)

አዝ፦ አምላኬ/ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ በአንተ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ወደር ፡ የለው ፡ ምህረትህ ፡ ፊትህ ፡ አቁሞኛል
ሁልጊዜ ፡ ማለዳ ፡ አዲስ ፡ ነህ ፡ ፍቅርህ ፡ አቻ ፡ የሌለው
ቸርነትህ ፡ በዛልኝ ፡ ሥምህን ፡ ላመስግነው (፪x)

ምህረትህ ፡ አቁሞኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
በልቤ ፡ ላመስግንህ ፡ ፈቅጄም ፡ ልገዛልህ (፪x)

አንደበቴን ፡ ልክፈት ፡ ጌታን ፡ ላመስግነው
ያዳነኝን ፡ አምላክ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ላርገው
መንፈሱ ፡ ሲነካካኝ ፡ የሥጋዬን ፡ አስረሳኝ
ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ ፡ አሃ ፡ አሃ (፪x)

አዝ፦ አምላኬ/ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ በአንተ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ወደር ፡ የለው ፡ ምህረትህ ፡ ፊትህ ፡ አቁሞኛል
ሁልጊዜ ፡ ማለዳ ፡ አዲስ ፡ ነህ ፡ ፍቅርህ ፡ አቻ ፡ የሌለው
ቸርነትህ ፡ በዛልኝ ፡ ሥምህን ፡ ላመስግነው (፪x)

ምህረትህ ፡ አቁሞኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
በልቤ ፡ ላመስግንህ ፡ ፈቅጄም ፡ ልገዛልህ (፪x)

ደስታዬ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ሰላም ፡ ሆነኸኛል
ከማንም ፡ ከምንም ፡ አንተ ፡ አርክተኸኛል
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ሁሌ ፡ ይከተሉኛል
ፍቅርህ ፡ በዝቶልኛል ፡ አሃ ፡ አሃ (፪x)