አምላኬ ፡ ነህ (Amlakie Neh) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 3.png


(3)

ሞኝነት ፡ ሆኖ ፡ አይደለም
(Mognenet Hono Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፪ (1999)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

እኔማ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ስንቱን ፡ አወራለሁ
የቱንስ ፡ አውርቼ ፡ የቱን ፡ እተዋለሁ
ያደረገልኝን ፡ ብቆጥር ፡ በየተራ
ከአዕምሮዬ ፡ በላይ ፡ ሆነ ፡ የእርሱ ፡ ሥራ

እኔማ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ስንቱን ፡ ላውራ
ከአዕምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ሥራ (፪x)

ክብር ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ክብር ፡ የኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

ተመስገን ፡ የምለው ፡ ካሳ ፡ ሆኖ ፡ አይደለም
የጌታን ፡ ውለታ ፡ የሚክሰው ፡ የለም
ክበርም ፡ የምለው ፡ ስለሚገባው ፡ ነው
ለውለታው ፡ ምላሽ ፡ ሊሰጥ ፡ የሚችል ፡ ማነው

እኔማ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ስንቱን ፡ ላውራ
ከአዕምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ሥራ (፪x)

አዝ፦ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ/ኢየሱሴ ፡ ወዳጄ ፡ እንከን ፡ የሌለህ
ፍቅርህ ፡ ለእኔ ፡ በቂ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ ታጠግበኛለህ (፪x)

ስለዚህ (፪x) ፡ በፍፁም ፡ ልቤ ፡ ጌታዬ ፡ ወድሃለሁ
ዘመኔን (፪x) ፡ እያከበርኩህ ፡ ለመኖር ፡ ወስኛለሁ (፪x)

ከእርሱ ፡ የሆነውን ፡ ለእርሱ ፡ አቀርባለሁ
እኔማ ፡ ምን ፡ አለኝ ፡ ምን ፡ እሰጠዋለሁ
እንዲሁ ፡ በፀጋው ፡ ፊቱ ፡ አቁሞኛል
ስለፈቀደልኝ ፡ አመስግን ፡ ብሎኛል

ስለፈቀደልኝ ፡ አሃሃ ፡ አመስግን ፡ ብሎኛል ፡ አሃሃ
ስለፈቀደልኝ ፡ ኦሆሆ ፡ አክብረኛል ፡ ብሎኛል ፡ አሃሃ

አዝ፦ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ/ኢየሱሴ ፡ ወዳጄ ፡ እንከን ፡ የሌለህ
ፍቅርህ ፡ ለእኔ ፡ በቂ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ ታጠግበኛለህ (፪x)

ስለዚህ (፪x) ፡ በፍፁም ፡ ልቤ ፡ ጌታዬ ፡ ወድሃለሁ
ዘመኔን (፪x) ፡ እያከበርኩህ ፡ ለመኖር ፡ ወስኛለሁ (፪x)