አለቴ ፡ ነው (Aletie New) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 3.png


(3)

ሞኝነት ፡ ሆኖ ፡ አይደለም
(Mognenet Hono Aydelem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፪ (1999)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

ምሕረቱ ፡ ገንኖ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ መልካም ፡ የሆነውን ፡ ቀን ፡ እንዳይ
ጨለማዬን ፡ ሁሉ ፡ አብርቶአል ፡ ሃዘን ፡ ትካዜም ፡ ከእኔ ፡ ርቋል
አንደበቴን ፡ ልክፈት ፡ ልናገር ፡ ያደረገልኝን ፡ ድንቅ ፡ ነገር
መልካምነቱ ፡ ህሉ ፡ ይሰማ ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ዓይኖርም ፡ ጨለማ

እርሱ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ እርሱ ፡ የእኔ ፡ እረኛ (፪)
ለምን ፡ እሰጋለሁ ፡ ለምን ፡ ልቤ ፡ ይፍራ

ዓለቴ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ መሠረቴ
እኔ ፡ ክፉን ፡ አልፈራም ፡ ኢየሱስ ፡ አለ ፡ በሕይወቴ

ሃላፊው ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ልረፍ ፡ እንጂ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ አሰጋኝ?
ብጨነቅ ፡ ባወጣው ፡ ባወርደው ፡ አንድም ፡ የለም ፡ የምጨምረው
ታማኝ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ እረኛ ፡ የማይደክም ፡ ከቶ ፡ የማይተኛ
ሃሣቤን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ ፡ ይረዳኛል ፡ አምኜዋለሁ

በቸርነቱ ፡ እጄን ፡ ይዞ ፡ ትላንትናን ፡ እንዳሳለፈኝ
ለዛሬውም ፡ አምላኬ ፡ አለልኝ ፡ ለምን ፡ ልፍራ ፡ ምን ፡ አስጨነቀኝ?
ምሕረቱና ፡ ቸርነቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ይከተሉኛል
አይተወኝም ፡ ለዘለዓለም ፡ ኢየሱሴ ፡ ቃል ፡ ገብቶልኛል