ሰማያዊ ፍቅር (Semayawi Fiker) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Lyrics.jpg


(7)

ልዘምር
(Lezemer)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2019)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

ህይወት እንዳገኘ ባምላክ ምህረት እንዳረፈ ሰው
በክፎቹ ጥላ ተሸሸሽጌ እዘምራለሁ
በአይነቱ የተለየ ሰማያዊ ፍቅር ይዞኛል
ግራ ቀኝ እንዳልል የኔ ወዳጅ ቤቱ ተክሎኛል

አይደል አጋጣሚ ይሄስ የአምላክ ፍቅር ነው
እንደኔ አይነቱን ሰው አጥቦ ልጅ ያደረገው
እዎ ነፍሴ ረክታለች በዘላለም ጌታ
ጨለማዬን ገፎ እስራቴን በፈታ

እንዲህ ነው አይባል ቃላት አይገልፀው
እየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ለኔ ያደርገው
እራርቶልኝ የህይወቴን ታሪክ ለውጥዋል
ባስደናቂው ፀጋ የእርሱ አድርጎኛል X2

ህይወት እንዳገኘ ባምላክ ምህረት እንዳረፈ ሰው
በክፎቹ ጥላ ተሸሸሽጌ እዘምራለሁ
በአይነቱ የተለየ ሰማያዊ ፍቅር ይዞኛል
ግራ ቀኝ እንዳልል የኔ ወዳጅ ቤቱ ተክሎኛል
 
ተመስግን እላለሁ ይክበር የሱስ ወዳጄ
ፍቅሩ ልቤን ገዝቶት ሰላም ፈሶ በደጄ
እውነት ነው ማዳኑ ሰንሰለት ይበጥሳል
ይኸው ምስክር ነኝ ምህረቱ በኔ ታይቷል

አገር ምድሩ ይስማ እየሱስ ያድናል
ካፈር ላይ አንስቶ ያዘምረኛል
እራርቶልኝ የህይወቴን ታሪክ ለውጥዋል
ባስደናቂው ፀጋ የሱ አድርጎኛል X2


ህይወት እንዳገኘ ባምላክ ምህረት እንዳረፈ ሰው
በክፎቹ ጥላ ተሸሸሽጌ እዘምራለሁ
በአይነቱ የተለየ ሰማያዊ ፍቅር ይዞኛል
ግራ ቀኝ እንዳልል የኔ ወዳጅ ቤቱ ተክሎኛል