ሰላም ፡ ይሰማኛል (Selam Yesemagnal) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Lyrics.jpg


(7)

ልዘምር
(Lezemer)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2019)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:55
ጸሐፊ (Writer): ዳዊት በቀለ
(Dawit Bekele
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

አዝ ፡ - ሰላሙን ጨምሮ ዘልቆ በህይወቴ ምንጩን አፈለቀ
የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ በውስጤ ፈሰሰ
አስደናቂው ፀጋ ጉልበቴ ሆነኝ ሰላም ይሰማኛል ባርኮቱ ደርሶኛል
እግዚአብሔር ለኔ ነው ይጠበቅኛል/ህይወት ሆኖኛል(2)

አምላክ ያዘጋጀው የሱስ ያለም ቤዛ ያለም መድሃኒት
እንዳልነዋወጥ ወጀቡ እንዳይጥለኝ ሆኖኝ መሰረት
መንፈሱ ሞልቶኛል በቤቱ ተክሎኛል
ዓለም የማይሰጠውን ሰላም ሰጥቶኛል (2)

አዝ ፡ - ሰላሙን ጨምሮ ዘልቆ በህይወቴ ምንጩን አፈለቀ
የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ በውስጤ ፈሰሰ
አስደናቂው ፀጋ ጉልበቴ ሆነኝ ሰላም ይሰማኛል ባርኮቱ ደርሶኛል
እግዚአብሔር ለኔ ነው ይጠበቅኛል/ህይወት ሆኖኛል(2)

የላቀ ደስታ ዓለምን የሚያስንቅ ሰላም ከሰማይ
በቃሉ ላመኑ ከጌታ ተሰጥቷል ከሱ ዘንድ ከላይ
ለኔም ይህን ደስታ ሰላም አግኝቻለሁ
እየተደነቅኩኝ አመልከዋለሁ (2)

አዝ ፡ - ሰላሙን ጨምሮ ዘልቆ በህይወቴ ምንጩን አፈለቀ
የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ በውስጤ ፈሰሰ
አስደናቂው ፀጋ ጉልበቴ ሆነኝ ሰላም ይሰማኛል ባርኮቱ ደርሶኛል
እግዚአብሔር ለኔ ነው ይጠበቅኛል/ህይወት ሆኖኛል(2)

እግዚአብሔር በቃሉ በመንፈሱ ሙላት የባረካችሁ
በደስታ እናምልከው እልልታው ይሰማ ይውጣ ድምፃችሁ
ጌታችን ይመስገን ይደርደር በገና
የሰላሙ ንጉስ እሱ/ኢየሱስ/ጌታ ነውና