መንፈሱ መጣ (Menfesu Meta) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Lyrics.jpg


(7)

አልበም
(6)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2019)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

መጣ መንፈሱ መጣ በእኔ አሄ
መጣ መንፈሱ መጣ በእኔ
የእግዚአብሔር መንፈስ መጣ በእኔ ኦሆ
መጣ መንፈሱ መጣ በእኔ
እንደተስፋ ቃሉ መንፈሱ መጣ በእኔ

የእግዚአብሔር ቸር ነው መንፈሱን ሞልቶኛል
አስተማሪዬ ነው በእውነት ይመራኛል
እንደተስፋ ቃሉ ከሰማይ የተሰጠኝ
ለወንጌል አደራ እንድበቃ ጉልበት ሆነኝ

አነቃቃኝ ጌታ እሳቱ ነደደ
የመንፈስ ቅዱስ ሃይል በኔ ላይ ወረደ
በአዲስ ቋንቋ ጸለይኩ ስጦታን ተቀበልኩኝ
አስደናቂ ክብሩን ማዳኑን መሰከርኩኝ

ከአርያም የሆነ ያገኘሁት መንፈስ
በባህሪው አምላክ ህይወትን የሚያድስ
አብ ወልድ መንፈስቅዱስ አንድ አምላክ ስላሴ
የእግዚአብሔር ይመስገን መጠለያ ለነብሴ