ማምለጫ (Mamlecha) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Lyrics.jpg


(7)

ልዘምር
(Lezemer)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2019)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

ማምለጫ አለኝ የጌታ ስም
ማምለጫ አለኝ ኦሆ የኢየሱስ ስም
ማምለጫ አለኝ የጌታ ስም
ማምለጫ አለኝ አሃ የኢየሱስ ስም
መዳኛዬ መዳኛዬ
ማምለጫዬ ነህ ማምለጫዬ
መዳኛዬ መዳኛዬ
ማምለጫዬ ነህ ማምለጫዬ

1. ስሙን ጠራሁ በጌታ አመንኩኝ
ከዘለዓለም ሞት አመለጥኩኝ
ዳግም ልደት ከላይ
ስልጣን ሰጠኝ የልጅነቱን
ከዘለዓለም ዘላቂ ህብረቱን
አዲስ ህይወት ሆነኝ
አመለጥኩኝ ኢየሱስ ቤዛ ሆነኝ (4)

ማምለጫ አለኝ የጌታ ስም (አዝ)

2. የጠላቴን ሰብሮ ወጥመዱን
ጌታ ቀድሞ አፍርሶ እቅዱን
ድልን አውርሶኛል
በወደደኝ አሸንፌአለሁ
ካስጨነቀኝ እጅ አምልጫለሁ
ምስጋና ለእግዚአብሔር
ጋሻ ሆነኝ በክንዱ ተደከፍኩኝ አሃ
ጋሻ ሆነኝ በክንዱ ተደገፍኩኝ (4)

ማመምለጫ አለኝ የጌታ ስም (አዝ)

3. ስሙ ለኔ የፀና አለቴ
አቁሞኛል ነው መሰረቴ
ሃያል የኔ ጌታ
ልቀኝለት ምስጋናን ላብዛ
ክቡር ደሙ ነፍሴን ለገዛ
ውዳሴ በረከት
ይሁንለት ለክቡር ስሙ ስግደት (4)

ማምለጫ አለኝ የጌታ ስም (አዝ)