ጠላቴን ፡ ድል ፡ ነሳሁት (Telatien Del Nesahut) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 2.jpg


(2)

በአንተ ፡ ብርታት
(Bante Bertat)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ (1997)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

ጌታዬ ባንተ አረ ስንቱን አለፍኩት
ስንቱን ታግዬ ስንቱን ባንተ ረታሁት
ጠላቴን ድል ነሳሁት ረገጥኩት አሸነፍኩት
     
    በሀሩር ጊዜ ጠንካራ ጥላ
    ሆነህ አይቻለሁ ለኔ ከለላ
    ነብሴንም ስታድን ከ ተኩላ
    ማይነቃነቅ ፅኑ ግንድ ሆንከኝ
    ጉያህ ሸሸገ እኔን ሰወርከኝ
    ጥበቃህን አበዛክልኝ

ጋሻ ነህ ለኔ በትር ምርኩዜ
በጦርነት ውስጥም በጭንቀት ጊዜ
ጠላቴን የምትጥል ሁል ጊዜ
ባንተ ክንድ ሁሉን ተሻግሪያለሁ
ጊንጥ እና እባቡን ረጋግጫለሁ
ማዕበሉን በድል አልፊያለሁ
    
    የጠላቴ ጦር አልደበረኝም
    ቢጮህ ቢያገሳ ከቶ አልነካኝም
    ወጀቡም ይዞ አላስቀረኝም
    መውጣት መግባቴ ባንተ ታጅቦ
    የክብርህ እሳት ዙሪያዬን ከቦ
    ቆሚያለሁ ህይወቴ አብቦ

አቤቱ አምላኬ ምን እልሀለሁ
ምንስ ብሰጥህ እክስሀለሁ
በህይወቴ ያደረከው ብዙ ነው
ልስጥህ እራሴን ተጠቀምብኝ
እንደወደድከው አድርገህ ስራብኝ
ክብርህን በኔ ግለጥብኝ