From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል (Daniel Amdemichael)
|
|
፪ (2)
|
አልበም (በአንተ ፡ ብርታት)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፲ ፱ ፻ ፺ (1997)
|
ቁጥር (Track):
|
፲ ፩ (11)
|
ርዝመት (Len.):
|
4:05
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች (Albums by Daniel Amdemichael)
|
|
ጌታየ : ባንተ : አረ : ሰንቱን : አለፍኩት
ሰንቱን : ታገዬ : ሰንቱን : ባንተ : ረታሁት
ጠላቴን ድል : ነሳሁት ፤ ረገጥኩት ፤ አሸነፍኩት
በሃሩር : ጊዜ : ጠንካራ : ጥላ
ሆነህ : አይቻለሁ : ለኔ : ከለላ
ነፍሴንም : ስታድን : ከተኩላ
ማይነቃነቅ : ጽኑ : ግንብ : ሆንከኝ
ጉያህ : ሸሽገህ : እኒን : ሰወርከኝ
ጥበቃህን : አበዛሀልኝ
ጌታየ : ባንተ : አረ : ሰንቱን : አለፍኩት
ሰንቱን : ታገዬ : ሰንቱን : ባንተ : ረታሁት
ጠላቴን ድል : ነሳሁት ፤ ረገጥኩት ፤ አሸነፍኩት
ጋሻ : ነህ : ለኔ : በትር : ምርኩዜ
በጦርነት : ውስጥም : በጭንቀት : ጊዜ
ጠላቴን : የምትጥል : ሁልጊዜ
ባንተ : ክንድ : ሁሉን : ተሻግሬአለሁ
ጊንጥና : እባቡን : ረጋግጫለሁ
ማዕበሉን : በድል : አልፌአለሁ
ጌታየ : ባንተ : አረ : ሰንቱን : አለፍኩት
ሰንቱን : ታገዬ : ሰንቱን : ባንተ : ረታሁት
ጠላቴን ድል : ነሳሁት ፤ ረገጥኩት ፤ አሸነፍኩት
የጠላቴ : ጦር : አልደፈረኘም
ቢጮህ : ቢያገሳ : ከቶ : አልነካኝም
ወጀቡም : ይዞ : አላስቀረኝም
መውጣት : መግባቴ : ባንተ : ታጅቦ
የክብርህ : አሳት : ዙሪያዬን : ከቦ
ቁሚያለሁ : ሕይወቴ : አብቦ
ጌታየ : ባንተ : አረ : ሰንቱን : አለፍኩት
ሰንቱን : ታገዬ : ሰንቱን : ባንተ : ረታሁት
ጠላቴን ድል : ነሳሁት ፤ ረገጥኩት ፤ አሸነፍኩት
አቤቱ : አምላኬ : ምን : እልሃልሁ
ምንስ : ብሰጥህ : እክስሃለሁ
ለሕይወቴ : ያረከው : ብዙ : ነው
ልስጥህ : ራሴን : ተጠቀምብኝ
እንደወደድከው : አርገህ : ስራብኝ
ክብርህን : በእኔ : ግለጥብኝ
ጌታየ : ባንተ : አረ : ሰንቱን : አለፍኩት
ሰንቱን : ታገዬ : ሰንቱን : ባንተ : ረታሁት
ጠላቴን ድል : ነሳሁት ፤ ረገጥኩት ፤ አሸነፍኩት
|