ለምን ፡ እንደዘገየ (Lemen Endezegeye) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 2.jpg


(2)

በአንተ ፡ ብርታት
(Bante Bertat)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ (1997)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

አዝ፦ ለምን ፡ እንደዘገየ ፡ ለእኔ ፡ ባይገባኝም
እጠብቀዋለሁ ፡ ፈፅሞ ፡ አይጥለኝም
ስጋዬን ፡ ልንከስ ፡ ልማፀነው
ፀሎቴን ፡ ሰምቶ ፡ እስኪመልሰው ፡ ጌታ

እጮሀለሁኝ ፡ እኔ ፡ አልታክትም
እስኪጎበኘኝ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም
እንባዬን ፡ ካይኔ ፡ እስኪያብስልኝ
እጠብቃለሁ ፡ እስኪደርስልኝ ፡ ጌታ ፡ እስኪያየኝ (፫x)

አዝ፦ ለምን ፡ እንደዘገየ ፡ ለእኔ ፡ ባይገባኝም
እጠብቀዋለሁ ፡ ፈፅሞ ፡ አይጥለኝም
ስጋዬን ፡ ልንከስ ፡ ልማፀነው
ፀሎቴን ፡ ሰምቶ ፡ እስኪመልሰው ፡ ጌታ

እስኪ ፡ እንደሀና ፡ እንባዬን ፡ ላፍስስ
መሪር ፡ ሀዘኔን ፡ በፊቱ ፡ ልግለፅ
ጨካኝ ፡ እንዳይደል ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ
ከእግሩ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ ልማፀነው ፡ ደጅ ፡ ልጥናው (፫x)

አዝ፦ ለምን ፡ እንደዘገየ ፡ ለእኔ ፡ ባይገባኝም
እጠብቀዋለሁ ፡ ፈፅሞ ፡ አይጥለኝም
ስጋዬን ፡ ልንከስ ፡ ልማፀነው
ፀሎቴን ፡ ሰምቶ ፡ እስኪመልሰው ፡ ጌታ

ፈተናው ፡ በዝቶ ፡ ቢያዝለኝም
ለሰይጣን ፡ ሀሳብ ፡ እጄን ፡ አልሰጥም
እርዳኝ ፡ እላለሁ ፡ በፊቱ ፡ ሆኜ
ድንቅ ፡ እንዲሰራ ፡ በእርሱ ፡ ታምኜ ፡ በረድኤቴ (፫x)

አዝ፦ ለምን ፡ እንደዘገየ ፡ ለእኔ ፡ ባይገባኝም
እጠብቀዋለሁ ፡ ፈፅሞ ፡ አይጥለኝም
ስጋዬን ፡ ልንከስ ፡ ልማፀነው
ፀሎቴን ፡ ሰምቶ ፡ እስኪመልሰው ፡ ጌታ

እታገሳለሁ ፡ ምልስ ፡ ይሆነኛል
ጌታ ፡ ጨክኖ ፡ መች ፡ ይተወኛል
የልመናዬ ፡ ፅዋዬ ፡ ሞልቶ
ይጎበኘኛል ፡ በጊዜው ፡ መጥቶ ፡ በቃ ፡ ብሎ (፫x)

አዝ፦ ለምን ፡ እንደዘገየ ፡ ለእኔ ፡ ባይገባኝም
እጠብቀዋለሁ ፡ ፈፅሞ ፡ አይጥለኝም
ስጋዬን ፡ ልንከስ ፡ ልማፀነው
ፀሎቴን ፡ ሰምቶ ፡ እስኪመልሰው ፡ ጌታ