ክብርህን (Kebrehen) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 2.jpg


(2)

ባንተ ብርታት
(Bante Bertat)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ (1997)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

ክብርህን : ለማየት : ነው : ጥማቴ
ስትነግስ : በሕይወቴ
አንተን : ለማገልገል : ነው : ውጥኔ
ባለቺኝ : ቀሪ : ዘመኔ

ርሃብ ፡ ጥማቱ ፡ ሳይገታቸው
ስደት ፡ ጭምር ፡ ሳያግዳቸው
ባሮችህ ፡ ለወንጌል ፡ ሮጠው
አልፈዋል ፡ ታሪክን ፡ ለውጠው

ክብርህን : ለማየት : ነው : ጥማቴ
ስትነግስ : በሕይወቴ
አንተን : ለማገልገል : ነው : ውጥኔ
ባለቺኝ : ቀሪ : ዘመኔ

ፍቃድህ ፡ ተፈጽሞ ፡ በኔ
ተከናውኖ ፡ እንዳየው ፡ ባይኔ
ይህ ፡ ነው ፡ መሻቴ ፡ ውድ ፡ ጌታዬ
አንተን ፡ ማገልገል ፡ መከታዬ

ክብርህን : ለማየት : ነው : ጥማቴ
ስትነግስ : በሕይወቴ
አንተን : ለማገልገል : ነው : ውጥኔ
ባለቺኝ : ቀሪ : ዘመኔ

የምድር ፡ ቆይታዬ ፡ አላማው
ጌታ ፡ አንተን ፡ ለማገልገል ፡ ነው
ስለዚህ ፡ ለወንጌል ፡ ልትጋ
ከዚ ፡ እስክስትወስደኝ ፡ አንተ ፡ ጋ

ክብርህን : ለማየት : ነው : ጥማቴ
ስትነግስ : በሕይወቴ
አንተን : ለማገልገል : ነው : ውጥኔ
ባለቺኝ : ቀሪ : ዘመኔ