እንደገና-በጊዜው ደረሰልኝ (Endegena) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 2.jpg


(2)

በአንተ ፡ ብርታት
(Bante Bertat)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ (1997)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

አዝ፦ ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ
       እርሱ አይቶ መች ጨከነብኝ
       ዳግም ተስፋዬን አደሰው
       እንባዬን ካይኔ አበሰው
       አምላኬ ታሪኬን ለዋወተው
እንደገና እንደገና እንደገና
እንደገና አቆመኝ /(፪x)

የኤርትራ ባህር በፊቴ እኔን ሊውጥ አፍጥጦ
የጠላቴ ጦር ከኋላ ሰይፉን መዞብኝ መጥቶ
ተስፋ ቆርጬ ስጨነቅ ጌታ ድንቅ አደረገ
የኤርትራን ባህር ከፍሎ እኔን በዚያ አሻገረ

    አዝ፦ ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ
       
በመንገዴ ላይ የቆመ ታላቅ ግዙፍ ተራራ
ቢገፉት የማይገፋ የሚያማርር መከራ
ተሻግሮ ማለፍ አቅቶኝ ኃይሌም ከውስጤ አልቆ
ኢየሱስ ከፊቴ አራቀው ሞቶ ተስፋዬን አደሰው

    አዝ፦ ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ

የሕይወት ዘመኔ መንምኖ ሞትም ዙሪያዬን ከቦኝ
ቀኔን ስጠብቅ ባልጋ ላይ ሕመም በጣም ጸንቶብኝ
እጅግ ቆዝሜ ሳነባ ደረሰልኝ አባባ
አዋጅን በአዋጅ ሻረ ሕይወትን ለኔ አበሰረ

    አዝ፦ ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ

ሃብቴ ንብረቴ ሁሉ አልቆ ዘመድ አዝማድም ርቆኝ
ከቁስሌ የተነሳ ሰው እጅጉን ተፀይፎኝ
ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር እንደገና አሰበኝ
ሕይወቴን አረሰረሰ ዳግም ምርኮዬን መለሰ

አዝ፦ ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ
       እርሱ አይቶ መች ጨከነብኝ
       ዳግም ተስፋዬን አደሰው
       እንባዬን ካይኔ አበሰው
       አምላኬ ታሪኬን ለዋወተው
እንደገና እንደገና እንደገና
እንደገና አቆመኝ /(፪x)