በድል ፡ ላይ ፡ ድልን ፡ ይዞ (Bedel Lay Delen Yezo) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 2.jpg


(2)

በአንተ ፡ ብርታት
(Bante Bertat)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ (1997)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

በድል ላይ ድልን ይዞ አሸንፎ የወጣ
 ስሙ የነገታት ንጉሥ የጌቶችም ጌታ ነው
 እንደ ጸሐይ ያበራል የለም የሚመስለው
 ጌታ እየሱስ ጌታ ነው አለም ሁሉ ይወቀው

በሰማይም በምድርም ፈቺ ያልተገኘለትን
ድንቁ ጌታ እየሱስ ነው የፈታው ማህተሙን
በረከት ይገባዋል ክብር ይሁን ለንጉሡ
ስግደትም ይገባዋል ስግደት ይሁን በፊቱ

እልፍ አላፍ መላእክቶች ቅኔን የቀኙለታል
ሽማግሌዎችም ፊቱ ወድቀው ይሰግዱለታል
በረከት ልትቀበል ይገባሃል ይሉታል
ምስጋናና ውዳሴ ለሱ ያቀርቡለታል

ሃያል ነው ክንደ ብርቱ የሚመስለው የሌለው
በውነት በጽድቅ የሚፈርድ ዲያቢሎስን የጣለ
የዘላለም ንጉስ ነው እየሱስ የከበረ
በሰማይም በምድር እጅጉን የገነነ