Daniel Amdemichael/Bante Bertat/Bante Bertat

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል ርዕስ ሁሉ ባንተ ነው አልበም በአንተ ብርታት

ከእኔ የሆነ ከእኔ የሆነ ከእኔ የሆነ ምን አለ ጌታ ከእኔ የሆነ ምን አለ አሃ አሃ ሁሉ በአንተ ነው ሁሉ በአንተ ነው ሁሉ በአንተ ነው ጌታ ኢየሱሴ ሁሉ በአንተ ነው የሆነው አሃ አሃ (፪x)

ፀንቼ መቆሜ ምህረትህ በዝቶ ነው (፪x) መውጣቴ መግባቴም ክንድህ ደግፎኝ ነው (፪x) አንድም ነገር የለም ከእኔ ነው የምለው (፪x) መላው እኔነቴ ኢየሱስ የአንተ ነው ጌታዬ የአንተ ነው

ከእኔ የሆነ ከእኔ የሆነ ከእኔ የሆነ ምን አለ ጌታ ከእኔ የሆነ ምን አለ 0አሃ ሁሉ በአንተ ነው ሁሉ በአንተ ነው ሁሉ በአንተ ነው ጌታ ኢየሱሴ ሁሉ በአንተ ነው የሆነው አሃ (፪x)

ሃዘኔን ለውጠህ ደስታን ሰጥተኸኛል (፪x) መከራዬን ሁሉ አስረስተኸኛል (፪x) ሁሉን ማከናወን መፈጸም ፡ ታውቃለህ (፪x) እስረኛውን ፈተህ ትከብርበታለህ (፪x)

አምላኬ ሆይ በአንተ ብርታት በአንተ አሃ አሃ ሃዘኔን እረሳሁት ያስተከዘኝ ያጨለማው አልፎ አሃ አሃ በአንተ ብርሃን አየሁኝ (፪x)

ይሁን ያልከው ሁሉ ሆኗል በሕይወቴ (፪x) አሁንም አንተው ነህ የምትመራኝ ረድኤቴ (፪x) በምንም አልፈራም ተደግፌሃለሁ (፪x) አንተ ሁሉ ቻይ ነህ በጥላህ አርፋለሁ (፪x)

አምላኬ ሆይ በአንተ ብርታት በአንተ አሃ አሃ ሃዘኔን እረሳሁት ያስለቀሰኝ / ያስጨነቀኝ ያ ጨለማው አልፎ አሃ አሃ በአንተ ብርሃን አየሁኝ (፪x)

ፍቅሩ የማይለወጥ ወረትን አይወድም (፪x) እስከዛሬ ድረስ ሰልችቶኝ አያውቅም (፪x) በምህረቱ ብዛት እየደጋገፈኝ (፪x) እዚህ ደርሻለሁ እስቲ አመስግኑልኝ (፪x)

አምላኬ ሆይ በአንተ ብርታት በአንተ አሃ አሃ ሃዘኔን እረሳሁት ያስጨነቀኝ ያ ጨለማው አልፎ አሃ አሃ በአንተ ብርሃን አየሁኝ (፪x)