ይረዳል (Yeredal) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 1.jpg


(1)

አንበሳ
(Anbesa)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፹ ፰ (1996)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

አዝ፦ ይረዳል ይደግፋል ጉልበት ይሆናል ጌታ (ኦሆሆ)
አይዞህ ባይ ወገን ደራሽ የምስኪኖች አለኝታ (ኦሆሆ) (፪x)

በምድር ላይ ለተገፋው አስታዋሽም ለሌለው
ሩህሩህ ነው ኢየሱሴ መጠጊያማ ይሆናል
የሃዘን ማቅን ቀዶ እንባንም ከዓይን አብሶ
ታሪክን ይለውጣል ዳግም በክብር ያቆማል

አዝ፦ ይረዳል ይደግፋል ጉልበት ይሆናል ጌታ (ኦሆሆ)
አይዞህ ባይ ወገን ደራሽ የምስኪኖች አለኝታ (ኦሆሆ) (፪x)

ሰብሳቢ ነው እረኛ ለሆነው መጻተኛ
ሁሉንም እንደየአመሉ በእቅፉ ይይዛል
አይቶ መች ያስችለዋል ተጠግቶም ይረዳል
እንደእርሱ ያለ ቸር ወዳጅ እረ ከየት ይገኛል

አዝ፦ ይረዳል ይደግፋል ጉልበት ይሆናል ጌታ (ኦሆሆ)
አይዞህ ባይ ወገን ደራሽ የምስኪኖች አለኝታ (ኦሆሆ) (፪x)

ትልቅ ነው ትንሽ አይል ሁሉንም በአንድ ይወዳል
ፍቅር ነው ኢየሱሴ መቼ ሰውን ይለያል
እርዳታውን ፈልጐ እርሱን ለተማጸነው
ታማኝ ነው የእኔ ጌታ የሚያጽናና መልስ አለው

አዝ፦ ይረዳል ይደግፋል ጉልበት ይሆናል ጌታ (ኦሆሆ)
አይዞህ ባይ ወገን ደራሽ የምስኪኖች አለኝታ (ኦሆሆ) (፪x)

የምድር ኑሮ አማሯችሁ ተስፋ የቆረጣችሁ
ኑ ዛሬ ወደ ኢየሱስ ዕረፍት ይሰጣችኋል
ሕይወትን ይለውጣል ተስፋን ያለመልማል
ምሬትን አስወግዶ በምሥጋና ይሞላል

አዝ፦ ይረዳል ይደግፋል ጉልበት ይሆናል ጌታ (ኦሆሆ)
አይዞህ ባይ ወገን ደራሽ የምስኪኖች አለኝታ (ኦሆሆ) (፪x)