ኦ ፡ ተመስገን (Oh Temesgen) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Daniel Amdemichael 1.jpg


(1)

አንበሳ
(Anbesa)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፹ ፰ (1996)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:01
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

አዝኦ ፡ ተመሥገን (፪x)
ስላደረክልኝ ፡ ድንቅ ፡ ነገር
ስላደረክልኝ ፡ መልካም ፡ ነገር
ምስኪኑን ፡ ረዳኸኝ ፡ ከትቢያ ፡ አነሳኸኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ (፪x)

የምህረት ፡ ዓይኖችህ ፡ ይከታተሉኛል
የበደሌን ፡ ብዛት ፡ ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ ሸፍኖታል
ሀዘንም ፡ ሲያጠቃኝ ፡ ከጐኔ ፡ ቆመሃል
መፅናናቴ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ አበርትተኸኛል (፪x)

አዝኦ ፡ ተመሥገን (፪x)
ስላደረክልኝ ፡ ድንቅ ፡ ነገር
ስላደረክልኝ ፡ መልካም ፡ ነገር
ምስኪኑን ፡ ረዳኸኝ ፡ ከትቢያ ፡ አነሳኸኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ (፪x)

ጌታዬ ፡ ተባረክ ፡ ሁሉም ፡ በአንተ ፡ ሆነ
አንድ ፡ ሁለት ፡ ብዬ ፡ የማወራው ፡ የለም ፡ ከእኔ ፡ የሆነ
እውነት ፡ ነፍሴን ፡ ላፍስስ ፡ ሥምህን ፡ ልወድሰው
የመዝሙሬ ፡ ዜማ ፡ ቅኔ ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላው (፪x)

አዝኦ ፡ ተመሥገን (፪x)
ስላደረክልኝ ፡ ድንቅ ፡ ነገር
ስላደረክልኝ ፡ መልካም ፡ ነገር
ምስኪኑን ፡ ረዳኸኝ ፡ ከትቢያ ፡ አነሳኸኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ (፪x)

በሰው ፡ የተናቀ ፡ የተጣለውን ፡ ሰው
መደነቂያ ፡ እንዲሆን ፡ ጌታ ፡ ለክብርህ ፡ አቆምከው
ብርታት ፡ ትሆናለህ ፡ ሞገስ ፡ ትሆናለህ
ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ጌታ/ኢየሱስ ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ (፪x)

አዝኦ ፡ ተመሥገን (፪x)
ስላደረክልኝ ፡ ድንቅ ፡ ነገር
ስላደረክልኝ ፡ መልካም ፡ ነገር
ምስኪኑን ፡ ረዳኸኝ ፡ ከትቢያ ፡ አነሳኸኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ (፪x)

አስደናቂው ፡ ፍቅርህ ፡ ከሳበኝ ፡ ጀምሮ
ያደረክልኝ ፡ ውለታ ፡ አያልቅም ፡ ተቆጥሮ
ጌታ ፡ የአንተ ፡ ሥራ ፡ በምን ፡ ቋንቋ ፡ ልግለፅ
ማለት ፡ የምችለው ፡ ይኸን ፡ ነው ፡ ኢየሱስ/ውድዬ ፡ ተባረክ (፪x)

አዝኦ ፡ ተመሥገን (፪x)
ስላደረክልኝ ፡ ድንቅ ፡ ነገር
ስላደረክልኝ ፡ መልካም ፡ ነገር
ምስኪኑን ፡ ረዳኸኝ ፡ ከትቢያ ፡ አነሳኸኝ
አልችልም ፡ እኔስ ፡ ልገልፀው ፡ ውለታህ ፡ በዛብኝ (፬x)