Daniel Amdemichael/Anbesa/Kewededkew

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል
ርዕስ ከወደድከው
አልበም አንበሳ
አዝ
ከወደድከው ምሥጋናዬን ጌታ ከተቀበልከው
እሰዋለሁ ዛሬም ነገም ጌታዬ አልሰለችም (፪x)
ቅዱስ ቅዱስ ከሚሉት እልፍ አላፍት መላዕክቶች
እኔንም ከደመርከኝ ከቤትህ ተቀኚዎች
መስዋዕቴን ከወደድከው ደስ ከተሰኸኘህበት
ይኸው ዝማሬ ኢየሱስ አንተው ከፍ በልበት
አዝ
ከወደድከው ምሥጋናዬን ጌታ ከተቀበልከው
እሰዋለሁ ዛሬም ነገም ጌታዬ አልሰለችም (፪x)
ጠቢባን አዋቂዎች በምድር ሞልተው እያሉ
ጥሪ አልደረሳቸውም ለዚህ ክብር አልታደሉም
ታላላቆቹን ንቀህ ምስኪኑን ታከብረዋለህ
ኧረ ተባረክ ኢየሱስ ፊት አይተህ መቼ ታደላለህ
አዝ
ከወደድከው ምሥጋናዬን ጌታ ከተቀበልከው
እሰዋለሁ ዛሬም ነገም ጌታዬ አልሰለችም (፪x)
ጠዋትም ማታም በአፌም ምሥጋናን እሰዋለሁ
የተቀደሰውን ሥምህን አከብራለሁ
ብቁ ሆኜ አይደለም ለዚህ የተገባሁኝ
ጌታ በምህረትህ ነው አንተው ይሁን ስላልከኝ
አዝ
ከወደድከው ምሥጋናዬን ጌታ ከተቀበልከው
እሰዋለሁ ዛሬም ነገም ጌታዬ አልሰለችም (፪x)
በህፃናት አፍም ምሥጋናን ታኖራለህ
የምስኪኑን አንደበት ዝማሬን ትሞላለህ
ይሁን አንተ ከፈቀድከው ይህንን ከወደድከው
እኔማ አይሰለቸኝም ጠዋት ማታ አዜማለሁ
አዝ
ከወደድከው ምሥጋናዬን ጌታ ከተቀበልከው
እሰዋለሁ ዛሬም ነገም ጌታዬ አልሰለችም (፪x)