Daniel Amdemichael/Anbesa/Eyesus New
< Daniel Amdemichael | Anbesa
ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል
ርዕስ ኢየሱስ ነው
አልበም አንበሳ
ኢየሱስ ነው ያከበረኝ
ጌታዬ ነው ከትቢያ ላይ ያነሳኝ
ዝም አልልም ለክብሩ ዘምራለሁ
ያከበረኝን /የባረከኝን/ ጌታ አከብረዋለሁ (፪x)
ጌታዬ ኢየሱስ ኤፍታህ ያለኝ ነኝ
ከሞት መልሶ ሕይወት የሰጠኝ
ዕዳዬ ተደምስሷል ነፃነቴም ታውጇል
ክብር ለሥሙ ይሁን ልቤ በኢየሱስ ረክቷል
አዝ
ኢየሱስ ነው ያከበረኝ
ጌታዬ ነው ከትቢያ ላይ ያነሳኝ
ዝም አልልም ለክብሩ ዘምራለሁ
ያከበረኝን /የባረከኝን/ ጌታ አከብረዋለሁ (፪x)
አንገት ያስደፋኝ ተሰበረ
ቅዱስ ጌታዬ በኔ ከበረ
ዛሬ ተፈትቻለው በምሥጋና ዘላለው
ሞገስ የሆነልኝን ኃያል ሥሙን ልባርከው (፪x)
አዝ
ኢየሱስ ነው ያከበረኝ
ጌታዬ ነው ከትቢያ ላይ ያነሳኝ
ዝም አልልም ለክብሩ ዘምራለሁ
ያከበረኝን /የባረከኝን/ ጌታ አከብረዋለሁ (፪x)
ሰላሙ እንደወንዝ ውስጤ ፈሰሰ
በረሃው ህይወቴም እረሰረሰ
ኢየሱሴ ወዶኛል ከፍ ከፍ አድርጎኛል
በሞገሱ ሸልሞ ለክብሩ አቁሞኛል (፪x)
አዝ
ኢየሱስ ነው ያከበረኝ
ጌታዬ ነው ከትቢያ ላይ ያነሳኝ
ዝም አልልም ለክብሩ ዘምራለሁ
ያከበረኝን /የባረከኝን/ ጌታ አከብረዋለሁ (፪x)
ጠላቴ ሰይጣን ወዴት አለህ
ሽክምህ ከላዬ ተንከባለለ
ከእጅህ ወጥቻለው የየሱሴ ሆኛለው
ለዘላለሙ ንጉስ ለሱ ተገዝቻለው (፪x)