From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አምላኬማ ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ዛሬም ፡ ይኖራል
ሳይለወጥ ፡ እየለወጠ ፡ ታሪክ ፡ ይሰራል
አምላኬማ ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ዛሬም ፡ ይኖራል
ሳይቀየር ፡ እየቀየረ ፡ ታሪክ ፡ ይሰራል
ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ እጅ
አይቻለሁኝ ፡ ሁሉን ፡ ሲያበጅ
ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ቃል
ያለ ፡ ምሰሶ ፡ ሰማይ ፡ ቆሟል
ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ እጅ
አይቻለሁኝ ፡ ሁሉን ፡ ሲያበጅ
ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ቃል
ስንት ፡ ደካማ ፡ በዚያ ፡ ቆሟል
አዝ፦ አቤት ፡ አቤት ፡ ሥራህ
እኔስ ፡ ጌታ ፡ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x)
ስለ ፡ ጌታ ፡ የሚባል ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ ኖሮ
እንዴት ፡ ልቤ ፡ ይግባ ፡ ሀዘን ፡ እንጉርጉሮ
እንደሰው ፡ ልጅ ፡ ሀሳብ ፡ አይደለም ፡ መንገዱ
ለበጎ ፡ ነው ፡ እንጀ ፡ እሱን ፡ ለወደዱ
አዝ፦ አቤት ፡ አቤት ፡ ሥራህ
እኔስ ፡ ጌታ ፡ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x)
ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ እጅ
አይቻለሁኝ ፡ ሁሉን ፡ ሲያበጅ
ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ቃል
ያለ ፡ ምሰሶ ፡ ሰማይ ፡ ቆሟል
ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ እጅ
አይቻለሁኝ ፡ ሁሉን ፡ ሲያበጅ
ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ቃል
ስንት ፡ ደካማ ፡ በዚያ ፡ ቆሟል
በመጀመሪያ ፡ በፍጥረት ፡ ዓለም
ግዑዝም ፡ ሕያው ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ የለም
ሁሉን ፡ ካመጣህ ፡ ከምንም ፡ ነገር
ዛሬም ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተናግረህ ፡ አይቀር
አዝ፦ አቤት ፡ አቤት ፡ ሥራህ
እኔስ ፡ ጌታ ፡ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x)
ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ሥም
ወደ ፡ ላይ ፡ አይሄድም ፡ ደፍሮ ፡ ማንም
ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መንፈስ
ወደ ፡ እውነት ፡ ሁሉ ፡ መርቶ ፡ ሚመልስ
ይሰራል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ሕግ
ፍትህ ፡ ያለበት ፡ ፍርድ ፡ የሚያደርግ
አዝ፦ አቤት ፡ አቤት ፡ ሥራህ
እኔስ ፡ ጌታ ፡ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x)
የተዋበና ፡ የተራቀቀ
የአምላኬ ፡ ሥራ ፡ እጅግ ፡ የላቀ
መፈጠር ፡ እንጂ ፡ መፍጠር ፡ ማን ፡ ችሏል
ማደስ ፡ ብቻ ፡ አይደል ፡ አዲስ ፡ ይሰራል
አዝ፦ አቤት ፡ አቤት ፡ ሥራህ
እኔስ ፡ ጌታ ፡ ወደድኩልህ/አየሁልህ (፪x)
|