የእኔ ፡ ነገር ፡ አላበቃም (Yenie Neger Alabeqam) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 4.jpg


(4)

ቃልህ ፡ ቃሌና ፡ ግብሬ
(Qaleh Qaliena Gebrie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

ተስፋዬ ፡ ተስፋዬ ፡ ነህ (፬x)
አላማዬ ፡ ግቤ ፡ የቀን ፡ የለት ፡ ህልሜ
መደምደሚያዬ ፡ ነህ ፡ ያለኸኝ ፡ ተስፋዬ (፪x)
የእኔ ፡ ነገር ፡ አላበቃም ፡ ጌታ ፡ ካለ ፡ አላለቀም
የእኔ ፡ ነገር ፡ አላበቃም ፡ ጌታ ፡ ካለ ፡ አላለቀም

በእኔና ፡ ሞት ፡ መሃል ፡ ተስፋ ፡ አለኝ (፪x)
አንድ ፡ እርምጃ ፡ ቀርቶኝ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ (፪x)
ስጋዬ ፡ እጅ ፡ ሰጥቶ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ (፪x)
ሰው ፡ ተስፋው ፡ ተሟጦ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ (፪x)

አዝ፦ የእኔ ፡ ነገር ፡ አላበቃም
ጌታ ፡ ካለ ፡ አላለቀም (፪x)

ቢቆረጥ ፡ ዛፍ ፡ ግንዱ ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x)
የውሃ ፡ ሽታ ፡ ካለ ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x)
ስሩ ፡ ጌታ ፡ ካለ ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x)
አለቱ ፡ ላይ ፡ ላለ ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x)

አዝ፦ የእኔ ፡ ነገር ፡ አላበቃም
ጌታ ፡ ካለ ፡ አላለቀም (፪x)

ቢሞት ፡ እንደአላዛር ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x)
ቢገነዝ ፡ ቢታሰር ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x)
ተከቶም ፡ ተቀብሮም ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x)
አልቆ ፡ ተደምድሞ ፡ ተስፋ ፡ አለ (፪x)

አዝ፦ የእኔ ፡ ነገር ፡ አላበቃም
ጌታ ፡ ካለ ፡ አላለቀም (፪x)