From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሲታመኑት ፡ የሚታመን
ቃሉን ፡ ደግሞ ፡ የማይበላ
የነገሩትን ፡ የማይረሳ
የለመኑትን ፡ የማይነሳ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ሁልጊዜ ፡ እውነተኛ
ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ለእኔ ፡ አለኛ
ኢየሱስ ፡ አይወድቅ ፡ ቃሉ ፡ መሬት
ኢየሱስ ፡ ታማኝ ፡ ላመኑበት
ሲታመኑበት ፡ ታማኝ (፬x)
ሲታመኑበት ፡ ታማኝ (፬x)
ረዳት ፡ በሌለበት ፡ በዚያ ፡ ቦታ
ማን ፡ ተስፋ ፡ ይደረጋል ፡ ያለጌታ
ዓይኔን ፡ የጣልኩበት ፡ አንድ ፡ ዋሴ
ጥያቄዬ ፡ ገባው ፡ እየሱሴ
ኢየሱሴ (፪x) ፡ የጥያቄ ፡ ሁሉ ፡ መልሴ
ኢየሱሴ (፪x) ፡ ዋስ ፡ ጠበቃ ፡ ነው ፡ ለነፍሴ
ሲታመኑት ፡ የሚታመን
ቃሉን ፡ ደግሞ ፡ የማይበላ
የነገሩትን ፡ የማይረሳ
የለመኑትን ፡ የማይነሳ (፪x)
እየሱስ ፡ ሁልጊዜ ፡ እውነተኛ
እየሱስ ፡ እሱ ፡ ለኔ ፡ አለኛ
እየሱስ ፡ አይወድቅ ፡ ቃሉ ፡ መሬት
እየሱስ ፡ ታማኝ ፡ ላመኑበት
ልቤን ፡ ወረሰና ፡ ወራሽ ፡ ሳይኖር
እንደኔማ ፡ ቢሆን ፡ ባልተገባኝ
ታሪኬን ፡ የሚያውቁ ፡ ጉድ ፡ ይበሉ
ሲያወጣኝ ፡ ሲያገባኝ ፡ እንደ ፡ ቃሉ
እንደ ፡ ቃሉ (፪x) ፡ ዝንፍ ፡ አይል ፡ አሰራሩ
እንደ ፡ ቃሉ ፡ ጌታ ፡ ቃሉ
አይሳሳት ፡ ስራው ፡ ምክሩ
ሲታመኑት ፡ የሚታመን
ቃሉን ፡ ደግሞ ፡ የማይበላ
የነገሩትን ፡ የማይረሳ
የለመኑትን ፡ የማይነሳ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ሁልጊዜ ፡ እውነተኛ
ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ለእኔ ፡ አለኛ
ኢየሱስ ፡ አይወድቅ ፡ ቃሉ ፡ መሬት
ኢየሱስ ፡ ታማኝ ፡ ላመኑበት
በቃሉ ፡ የሰፈረው ፡ እንደዚህ ፡ ነው
የእኔ ፡ ነገር ፡ እኮ ፡ በእጁ ፡ ነው
አልሞትም ፡ በህይወት ፡ ልኑር ፡ እንጂ
ከበቂ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ እጅ
የአንተ ፡ እጅ (፪x) ፡ ከሰው ፡ በላይ ፡ የሚመች
የአንተ ፡ እጅ (፪x) ፡ መች ፡ ይጥላል ፡ ሚያነሳ ፡ እንጂ
ሲታመኑት ፡ የሚታመን
ቃሉን ፡ ደግሞ ፡ የማይበላ
የነገሩትን ፡ የማይረሳ
የለመኑትን ፡ የማይነሳ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ሁልጊዜ ፡ እውነተኛ
ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ለእኔ ፡ አለኛ
ኢየሱስ ፡ አይወድቅ ፡ ቃሉ ፡ መሬት
ኢየሱስ ፡ ታማኝ ፡ ላመኑበት
|