ሰላም ፡ አለኝ (Selam Alegn) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 4.jpg


(4)

ቃልህ ፡ ቃሌና ፡ ግብሬ
(Qaleh Qaliena Gebrie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሰላም ፡ አለኝ (፬x)

ሀዘን ፡ የሚገፍ ፡ ሰላም ፡ ሰላም ፡ አለኝ
አእምሮን ፡ የሚያልፍ ፡ ሰላም ፡ ሰላም ፡ አለኝ
አልሰኝም ፡ ቅር ፡ ሰላም ፡ ሰላም ፡ አለኝ
ልቤ ፡ አይሰበር ፡ ሰላም ፡ ሰላም ፡ አለኝ

አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሰላም ፡ አለኝ (፬x)

በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ እንደሚኖር ፡ ሰው (፪x)
ሁሉን ፡ በሚችለው ፡ እሸሸጋለሁ (፪x)
አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ምን ፡ እሆናለሁ (፪x)
አምላክ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ ምን ፡ ያገኘኛል (፪x)
አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ መታመኛዬ (፪x)
አምላክ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ ሰላም ፡ ደስታዬ (፪x)

አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሰላም ፡ አለኝ (፬x)

ነገስ ፡ አልልም ፡ ሰላም ፡ ሰላም ፡ አለኝ
ለእራሱ ፡ ይጨነቅ ፡ ሰላም ፡ ሰላም ፡ አለኝ
ክፋት ፡ ቢሰንቅ ፡ ሰላም ፡ ሰላም ፡ አለኝ
አይበርደኝ ፡ አልሞቅ ፡ ሰላም ፡ ሰላም ፡ አለኝ

አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሰላም ፡ አለኝ (፬x)

አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ምን ፡ እሆናለሁ (፪x)
አምላክ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ ምን ፡ ያገኘኛል (፪x)
አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ መታመኛዬ (፪x)
አምላክ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ ሰላም ፡ ደስታዬ (፪x)

ሰራዊት ፡ ቢሰፍር ፡ ሰላም ፡ ሰላም ፡ አለኝ
ሰልፍ ፡ ቢነሳ ፡ ሰላም ፡ ሰላም ፡ አለኝ
ምድር ፡ ቢናወጥ ፡ ሰላም ፡ ሰላም ፡ አለኝ
ሰላም ፡ አለኝ ፡ ሰላም ፡ ሰላም ፡ አለኝ (፪x)

አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሰላም ፡ አለኝ (፬x)