From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አንተ ፡ ባትደረስ ፡ ባታየኝ ፡ ኖሮ
አይዞህ ፡ ያለኝ ፡ ሰው ፡ ድንገት ፡ ተሰብሮ
ባበቃ ፡ ነበር ፡ እዛ ፡ ላይ ፡ እኔስ ፡ ታሪኬ
አዋጅ ፡ ባይሻር ፡ የሞቴ ፡ ባንተ ፡ ባምላኬ (፪x)
ሰው ፡ አለኝ ፡ አይደለም ፡ ያልኩት
ጌታን ፡ ነው ፡ እኔስ ፡ የያዝኩት (፬x)
መመኪያዬ ፡ መታመኛ ፡ ነው
እሱን ፡ ይዤ ፡ ታዲያ ፡ እንዴት ፡ ፈራለሁ (፪x)
ሰው ፡ አለኝ ፡ አይደለም ፡ ያልኩት
ጌታን ፡ ነው ፡ እኔስ ፡ የያዝኩት (፪x)
በስብርባሪውም ፡ እደርሳለሁ ፡ እንጂ
አልቀርም ፡ ስምጬ ፡ ይዤ ፡ የአንተን ፡ እጅ
ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ
ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ ሆ
ይሞታል ፡ እያሉ ፡ ይጠባበቃሉ
እሱን ፡ ይዞ ፡ ያፈረ ፡ ማንን ፡ ሰው ፡ ያውቃሉ
ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ
ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ ሆ
መመኪያዬ ፡ መታመኛ ፡ ነው
እሱን ፡ ይዤ ፡ ታዲያ ፡ እንዴት ፡ ፈራለሁ (፪x)
በእርግጥ ፡ ወጀብ ፡ ካለ ፡ ታንኳ ፡ አይለቀቅም
ና ፡ ካለኝ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ልቀር ፡ አላስብም
ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ
ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ ሆ
በድካም ፡ በብርታት ፡ አሳልፎ ፡ የማይሰጥ
እሱን ፡ መያዝ ፡ እንጂ ፡ ማዕበሉን ፡ ለማምለጥ
ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ
ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ ሆ
ሰው ፡ አለኝ ፡ አይደለም ፡ ያልኩት
ጌታን ፡ ነው ፡ እኔስ ፡ የያዝኩት (፬x)
ለዚህች ፡ አጭር ፡ ዘመን ፡ ለዚህች ፡ አጭር ፡ ጊዜ
ቅርት ፡ ይበል ፡ ሁሉም ፡ ዘላለሜን ፡ ይዤ
ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ
ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ ሆ
አንዱም ፡ አላረካኝ ፡ አንዱም ፡ ውስጤ ፡ አልገባ
አንተን ፡ ስይዝህ ፡ ነው ፡ የደረቀው ፡ የኔ ፡ እንባ
ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ
ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ ሆ
መመኪያዬ ፡ መታመኛ ፡ ነው
እሱን ፡ ይዤ ፡ ታዲያ ፡ እንዴት ፡ ፈራለሁ (፪x)
|