ኢየሱሴ ፡ የምታልፈው (Eyesusie Yemetalfew) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 4.jpg


(4)

ቃልህ ፡ ቃሌና ፡ ግብሬ
(Qaleh Qaliena Gebrie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

አለም ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ እያረፈ
ይኼ ፡ ጌታ ፡ በዚህ ፡ እያለፈ
ዝም ፡ አልልም ፡ እጮሀለሁ
የዳዊት ፡ ልጅ ፡ እለዋለሁ (፪x)

እየሱሴ ፡ የምታልፈው
የቆጠርከኝ ፡ እኔን ፡ ከሰው
ባክህ ፡ ንካኝ ፡ አይኔን/ግባ ፡ ቤቴን ፡ ፈውሰው (፪x)

ዝም ፡ አልልም ፡ አታልፍም/ደርሶልኝ ፡ ቀኔ
ዝም ፡ አልልም ፡ ሳይበራ/ልትበራ ፡ አይኔ
ዝም ፡ አልልም ፡ አዳኜ ፡ መጥቶ
አየዋለሁ ፡ አይኔ ፡ ተከፍቶ (፪x)

የሚጋፋ ፡ ግን ፡ የማይነካ
የሚከፋው ፡ ለሰው ፡ ሲሳካ
ተው ፡ ቢለኝም ፡ አልተውም ፡ እኔ
ጨልሞብኝ ፡ አይለቅ ፡ ዘመኔ (፪x)

እየሱሴ ፡ የምታልፈው
የቆጠርከኝ ፡ እኔን ፡ ከሰው
ባክህ ፡ ንካኝ ፡ አይኔን/ግባ ፡ ቤቴን ፡ ፈውሰው (፪x)

ዝም ፡ አልልም ፡ አታልፍም/ደርሶልኝ ፡ ቀኔ
ዝም ፡ አልልም ፡ ሳይበራ/ልትበራ ፡ አይኔ
ዝም ፡ አልልም ፡ አዳኜ ፡ መጥቶ
አየዋለሁ ፡ አይኔ ፡ ተከፍቶ (፪x)

እርሱ ፡ ጠርቶ ፡ ምን ፡ ይለመናል
ብር ፡ ወርቅማ ፡ ሰውም ፡ ይሰጣል
ልከተልሀ ፡ ፈውስ ፡ አይኔን
መብራት ፡ የኔን ፡ ሰውነቴን (፪x)

በሰፈሬ ፡ በመንደሬ
ሰምቻለሁ ፡ መልካም ፡ ወሬ
መታሰሬ ፡ መታወሬ
ታሪክ ፡ ይሁን ፡ ያብቃ ፡ ዛሬ
አንዴ ፡ ልይህ ፡ አንተን ፡ ዛሬ (፪x)

እየሱሴ ፡ የምታልፈው
የቆጠርከኝ ፡ እኔን ፡ ከሰው
ባክህ ፡ ንካኝ ፡ አይኔን/ግባ ፡ ቤቴን ፡ ፈውሰው (፪x)

ዝም ፡ አልልም ፡ አታልፍም/ደርሶልኝ ፡ ቀኔ
ዝም ፡ አልልም ፡ ሳይበራ/ልትበራ ፡ አይኔ
ዝም ፡ አልልም ፡ አዳኜ ፡ መጥቶ
አየዋለሁ ፡ አይኔ ፡ ተከፍቶ (፪x)