አስበኝ (Asebegn) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 4.jpg


(4)

ቃልህ ፡ ቃሌና ፡ ግብሬ
(Qaleh Qaliena Gebrie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ቃሌን ፡ ስማ
ፀሎቴን ፡ አድምጥ ፡ ልመናዬ ፡ ይድረስልኝ
አንዴ ፡ አስበኝ ፡ ናልኝ ፡ አስበኝ
በአንተ ፡ ብቻ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ
አንዴ (፪x) ፡ አስበኝ
ሌላ ፡ ጥያቄ ፡ መሻት ፡ የለኝ

ፀጋህ ፡ ሳያንሰኝ ፡ ምህረትሀ ፡ ሳይጎድል
ምነው ፡ መዛሌ ፡ ምነው ፡ መታለል
መንገድህ ፡ ባይሆን ፡ እንደመንገዴ
እድልን ፡ ስጠኝ ፡ አስበኝ ፡ አንዴ

አዝ፦ አስበኝ ፡ አስበኝ ፡ አንዴ ፡ አስበኝ (፪x)
አሳልፈህ ፡ ለፈቃዴ ፡ ከቶ ፡ አትስጠኝ (፪x)

አትሰብር ፡ ከቶ ፡ ቅጥቅጥ ፡ ሸምበቆ
መንፈሱ ፡ ደቆ ፡ ሰው ፡ ካንተ ፡ ርቆ
አታጠፋውም ፡ ሚጤሰውን ፡ ጧፍ
ግን ፡ ሳታስበኝ ፡ ጊዜው ፡ እንዳያልፍ

አዝ፦ አስበኝ ፡ አስበኝ ፡ አንዴ ፡ አስበኝ (፪x)
አሳልፈህ ፡ ለፈቃዴ ፡ ከቶ ፡ አትስጠኝ (፪x)

አሀአሀሀሀ ፡ አስበኝ
አሀአሀሀ ፡ አስበኝ
አስበኝ ፡ ጌታ ፡ አሀሀሀሀ

ከአለት ፡ ንቃቃት ፡ ተሸሽጌያለሁ
ክረምቱ ፡ ሲያልፍ ፡ ያኔ ፡ ወጣለሁ
ለምትል ፡ ነፍሴ ፡ ለተጨነቀች
የአንተን ፡ ጉብኝት ፡ አንዴ ፡ ትላለች

አዝ፦ አስበኝ ፡ አስበኝ ፡ አንዴ ፡ አስበኝ (፪x)
አሳልፈህ ፡ ለፈቃዴ ፡ ከቶ ፡ አትስጠኝ (፪x)

ያለቦታዬ ፡ ቦታን ፡ አግኝቼ
በምድያም ፡ ሀገር ፡ ሰውን ፡ ፈርቼ
ተነስ ፡ የሚል ፡ ድምፅ ፡ አንተ ፡ ፅኔ ፡ ሀያል
ስታስብ ፡ እንጂ ፡ ከየት ፡ ይሰማል

አዝ፦ አስበኝ ፡ አስበኝ ፡ አንዴ ፡ አስበኝ (፪x)
አሳልፈህ ፡ ለፈቃዴ ፡ ከቶ ፡ አትስጠኝ (፪x)

አስበኝ ፡ እንደቃልህ
አሀሀሀ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እኔን ፡ አንዴ ፡ አስበኝ

አትሰብር ፡ ከቶ ፡ አስበኝ
መንፈሱ ፡ ደቆ ፡ እንደቃልህ
አታጠፋውም ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
ግን ፡ ሳታስበኝ ፡ ጊዜው ፡ እንዳያልፍ

አዝ፦ አስበኝ ፡ አስበኝ ፡ አንዴ ፡ አስበኝ (፪x)
አሳልፈህ ፡ ለፈቃዴ ፡ ከቶ ፡ አትስጠኝ (፪x)