አዳነኝ (Adanegn) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 4.jpg


(4)

ቃልህ ፡ ቃሌና ፡ ግብሬ
(Qaleh Qaliena Gebrie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

ታሪክ ፡ አይደል ፡ ተረት
የሰራው ፡ በኔ ፡ ሕይወት
ብዙ ፡ ሀያላን ፡ እያሉ
ወዶ ፡ አዳነኝ ፡ በቃሉ

አዝ፦ አዳነኝ ፡ ወደደኝና ፡ አወጣኝ ፡ ወደ ፡ ሰፊው ፡ ስፍራ
አዳነኝ (፪x) ፡ ወደ ፡ ሰፊው ፡ ስፍራ ፡ አወጣኝ
አዳነኝ (፪x) ፡ ወደ ፡ ፍቅሩ ፡ መንግስት ፡ አገባኝ

አስቤው ፡ አይደልም ፡ አቅጄ (፪x)
አስቦልኝ ፡ እንጂ ፡ ተወድጄ (፪x)
የሞት ፡ ወጥመድ ፡ ቀርቦ ፡ ሊይዘኝ
ኪዳኑ ፡ ምህረቱ ፡ አዳነኝ (፪x)

የመስቀሉ ፡ ቃል ፡ ለሚጠፉት ፡ ሞኝነት
ለእኔ ፡ ግን ፡ መቆም ፡ የመኖሬ/የመዳኔ ፡ ምክንያት

አዝአዳነኝ (፪x) ፡ አወጣኝ ፡ ወደ ፡ ሰፊው ፡ ስፍራ
አዳነኝ (፪x) ፡ ወደ ፡ ፍቅሩ ፡ መንግስት ፡ አገባኝ

እንደማልችል ፡ አውቆ ፡ በራሴ (፪x)
ታዳጊ ፡ ሆነላት ፡ ለነፍሴ (፪x)
ነጠቀኝ ፡ ከአፋፉ ፡ ከሞት (፪x)
አረገኝ ፡ ካህኑ ፡ ለፍቅሩ ፡ መንግስት (፪x)

አዝ፦ አዳነኝ (፪x) ፡ አስቀመጠኝ ፡ ጐኑ ፡ በአብ ፡ ቀኝ
አዳነኝ (፪x) ፡ የመንግስቱ ፡ ወራሽ ፡ አረገኝ

ታሪክ ፡ አይደል ፡ ተረት
የሰራው ፡ ለኔ ፡ ሕይወት
ብዙ ፡ ኃያላን ፡ እያሉ
ወዶ ፡ አዳነኝ ፡ በቃሉ

አዝ፦ አዳነኝ ፡ ወደደኝ ፡ አወጣኝ ፡ ወደ ፡ ሰፊው ፡ ስፍራ
አዳነኝ (፪x) ፡ ወደ ፡ ሰፊው ፡ ስፍራ ፡ አወጣኝ
አዳነኝ (፪x) ፡ ወደ ፡ ፍቅሩ ፡ መንግስት ፡ አገባኝ

የመስቀሉ ፡ ቃል ፡ ለሚጠፉት ፡ ሞኝነት
ለእኔ ፡ ግን ፡ መቆም ፡ የመኖሬ/የመዳኔ ፡ ምክንያት (፪x)