አቤቱ ፡ ነፍሴ (Abietu Nefsie) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 4.jpg


(4)

ቃልህ ፡ ቃሌና ፡ ግብሬ
(Qaleh Qaliena Gebrie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

አምላኬ ፡ ፊትህን ፡ መቼ ፡ አየዋለሁ
ውዴ ፡ ሆይ ፡ አንተስ ፡ ጋር ፡ መቼ ፡ እደርሳለሁ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ናፈቀች (፪x)
እንደ ፡ ዋላ ፡ ውኃ ፡ እንደተጠማች (፪x)

ውኃም ፡ እንጨትም ፡ በሌለበት
ነፍሴ ፡ ተጠማች ፡ የአምላኳን ፡ ፊት
ሥጋዬም ፡ ናፍቃ ፡ በምድረበዳ
ኃይልህን ፡ ክብርህን ፡ እንድታይ ፡ ወዳ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ናፈቀች (፪x)
እንደ ፡ ዋላ ፡ ውኃ ፡ እንደተጠማች (፪x)

ወዳንተ ፡ ወዳንተ ፡ እገሰግሳለሁ (፬x)

በመኝታዬ ፡ አስብሀለሁ
ማለዳ ፡ ቀትር ፡ አወራሀለሁ
ነፍሴ ፡ ከኋላ ፡ ተከተለችህ
ውዴ ፡ ወዳጄ ፡ ፍቅሬ ፡ አለችህ

አምላክ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ዘወትር ፡ ሲል
እምባዬ ፡ በዝቶ ፡ ምግብ ፡ ሲሆነኝ
ወደ ፡ ምሥጋና ፡ ማደሪየህ ፡ ልግባ
ነፍሴ ፡ እንድትጠግብ ፡ አንተን ፡ አስባ

አዝ፦ አቤቱ ፡ ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ናፈቀች (፪x)
እንደ ፡ ዋላ ፡ ውኃ ፡ እንደተጠማች (፪x)