አባባ (Ababa) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 4.jpg


(4)

ቃልህ ፡ ቃሌና ፡ ግብሬ
(Qaleh Qaliena Gebrie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

የሲዖል ፡ ጣር ፡ ሲይዘኝ
የሞት ፡ ወጥመድ ፡ ሲከበኝ
ስማኝ ፡ ስለው ፡ አባባ
ጩኸቴ ፡ ጆሮው ፡ ገባ ፡ አባባ
አባቴ ፡ ቀንዴ ፡ ነው ፡ ረድኤቴ
አባባዬ ፡ አባባ ፡ ጩኸቴ ፡ ጆሮው ፡ ገባ ፡ አባባ

እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ አምባዬ (፪x)
ትምክህቴ ፡ ጦሬ ፡ ነው ፡ ጋሻዬ (፪x)

ሰማይ ፡ ዝቅ ፡ አለ ፡ አምላኬ ፡ ወረደ (፪x)
ከአፉ ፡ እሳት ፡ እየነደደ (፪x)

ቁጣው ፡ ወጣ ፡ ጌታዬ ፡ በራ
በቀል ፡ የእርሱ ፡ የአምላኬ ፡ የእርሱ ፡ ሥራ
ለሚጠላኝ ፡ ወደረኛ
ወየውለት ፡ ጌታ ፡ መጣልኛ
ለሚጠላኝ ፡ ወደረኛ
ወየውለት ፡ ዘመን ፡ መጣልኛ

በአንተ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላላሁ
በጭፍራው ፡ ላይ ፡ እሮጣለሁ
አጥፋ ፡ ብሎኝ ፡ አውጥቶአቸው
ቀስተ ፡ ሰይፉን ፡ አሳያቸው
በቀኝህ ፡ አስር ፡ ሺህ ፡ ወደቁ
ሳይቀርቡ ፡ ሺዎችም ፡ አለቁ
እንደጋሻ ፡ እውነቱ ፡ ከበበኝ
ከፍላፃ ፡ አስጣለኝ

ሰማይ ፡ ዝቅ ፡ አለ ፡ አምላኬ ፡ ወረደ (፪x)
ከአፉ ፡ እሳት ፡ እየነደደ (፪x)

ኃይልን ፡ ለበስኩ ፡ አስታጠቀኝ
የጠላቴን ፡ ጀርባ ፡ ሰጠኝ
እንደ ፡ ጭቃ ፡ ረገጥኳቸው
እንደ ፡ ትቢያ ፡ ፈጨኋቸው
መክበቡን ፡ ዙሪያዬን ፡ ከበቡኝ
አታልፍም ፡ ስንዝርም ፡ ብለውኝ
በስቃያቸው ፡ ላይ ፡ እየሳቅኩ
በሥምህ ፡ አሸነፍኩ

ቁጣው ፡ ወጣ ፡ ጌታዬ ፡ በራ
በቀል ፡ የእርሱ ፡ የአምላኬ ፡ የእርሱ ፡ ሥራ
ለሚጠላኝ ፡ ወደረኛ
ወየውለት ፡ ጌታ ፡ መጣልኛ
ለሚጠላኝ ፡ ወደረኛ
ወየውለት ፡ ዘመን ፡ መጣልኛ