From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሲወራ ቢዋል ቢታደር
አይገልፅም ያምላኬን ፍቅር
ሲወራ ቢዋል ቢታደር
አይበቃም ላየሁት ነገር
ፍቅሩን ልከፍል በምን አቅሜ
በልቤ ገብቶ በስጋ ደሜ
ካይምሮ በላይ ሆኖብኝ ፍቅሩ
አይሰለቸኝም መዋል ማደሩ
በልቤ ዙፍኑን የሰራ
አያልቅም ስለሱ ቢወራ
ታሪኬን በመስቀል የሰራው
አያልቅም ስለሱ ቢወራ
ይወራ የእሱ ፍቅር
ይወራ አንድም ሳይቀር
ይወራ የእሱ ሰላም
ይወራ አልቀነሰም
ይወራ የእሱ ምሕረት
ይወራ ነው በየእለት
ይወራ የእሱ ቸርነት
ይወራ ያለ መሰልቸት
ስሙልኝ ስሙልኝ ስለዚህ ወዳጅ
ማረከኝ በፍቅሩ አይደለም በግዳጅ
እዩልኝ እዩልኝ ይህንን ትሁት
ማይወደውን ወዶ ለፍቅር የሚሞት
ይወራ የእሱ በጎነት
ይወራ በደረስኩበት
ይወራ የእሱ ቅንነት
ይወራ ውሸት የለበት
ይወራ ሰውን መውደዱ
ይወራ ያመኑት ቢከዱ
ይወራ በየሰበቡ
ይወራ አዛኝ ነው ልቡ
ይወራ ፡ ይወራ ፡ ይወራ
እስትፍስ ባለው
ይወራ ጌታ በረዳው
ይወራ አንደበት ባለው
ይወራ እሱ ባገዘው
ሲወራ ቢዋል ቢታደር
አይበቃም ላምላኬ ፍቅር
ሲወራ ቢዋል ቢታደር
አይበቃም ላየውት ነገር
ፍቅሩን ልከፍል በምን አቅሜ
በልቤ ገብቶ በስጋ ደሜ
ካይምሮ በላይ ሆኖብኝ ፍቅሩ
አይሰለቸኝም መዋል ማደሩ
ስሙልኝ ፡ ስሙልኝ ፡ ስለዚህ ፡ ጌታ
በወረት ተይዞ አይለይም ላፍታ
እዩልኝ እዩልኝ ይሄንን ደግ
ክፉ ላረገበት መልካም የሚያረግ
ከውርደት ለክብር የጠራኝ
ደንዳናውን ልቤን የገራ
ይወራ የእሱ በጎነት
ይወራ በደረስኩበት
ይወራ የእሱ ቅንነት
ይወራ ውሸት የለበት
ይወራ ሰውን መውደዱ
ይወራ የመኑት ቢከዱ
ይወራ በየሰበቡ
ይወራ አዛኝ ነው ልቡ
ስሙልኝ ስሙልኝ ይሄንን ጌታ
በወረት ተይዞ አይለይም ላፍታ
እዩልኝ እዩልኝ ይሄንን ደግ
ክፉ ላረገበት መልካም የሚያረግ
|