ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (Eyesus Becha new) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አልበም
(ሌላ ሌላ ሌላ ምነው በኖረና)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

ጉልበት ስሙን ሰምቶ የሚምበረከክለት ማነው ኢየሱስ ነው ማነው
ከላይ የተሰጠ ክብር የሞላበት ማነው ኢየሱስ ነው ማነው
የፀና ግንብ ነው ላልፀናው ነገሬ ማነው ኢየሱስ ነው ማነው
እሱ ሚጠራበት ለኔ ደግሞ ክብሬ ማነው ኢየሱስ ነው ማነው

ኢየሱስ ነው 12X
ኢየሱስ ብቻ ነው ኢየሱስ 2X ስሙ
ኢየሱስ ብቻ ነው ኢየሱስ 2X

ከማውቃቸው ሁሉ ስሙ ይለያል
ሲጠሩት እንደ ማር ይጣፍጣል
እንደስሙ ወድያው የሚወዱት
ከሌሎች ስም በላይ የሚመርጡት 2X

ኢየሱስ ብቻ ነው ኢየሱስ 2X ስሙ
ኢየሱስ ብቻ ነው ኢየሱስ 2X

የማዕዘኑ ራስ የስም መጨረሻ
ማነው ኢየሱስ ነው ማነው
የፍጥረት ጀማሪ የታሪክ መነሻ
ማነው ኢየሱስ ነው ማነው
ቢጠራ የሚመልስ ከቶ የማያፍሩበት
ማነው ኢየሱስ ነው ማነው
ስሙ የማይጠፋ እንከን ተገኝቶበት
ማነው ኢየሱስ ነው ማነው

ኢየሱስ ብቻ ነው ኢየሱስ 2X ስሙ
ኢየሱስ ብቻ ነው ኢየሱስ 2X

ኢየሱስ ነው 8X

የስንቱ ሲያረጅ ጉልበት አጥቶ
ስሙን ሲቀይሩት ወዙ ወጥቶ
ከስም ሁሉ በላይ የተሰጠ
የኢየሱሴ ስም ግን ሁሌ አዲስ ነው 2X

ስሙ ኢየሱስ ነው ውስጡ ጉልበት አለው
ስሙ መሲሑ ነው ለእኔስ መዳኛ ነው
ስሙ ኢየሱስ ነው ውስጡ ጉልበት አለው
ስሙ አንበሳ ነው የሚያስፋራ ስም ነው

ስሙ ኢየሱስ ነው ውስጡ ጉልበት አለው
ስሙ መሲሑ ነው ለእኔስ መዳኛ ነው
ስሙ ኢየሱስ ነው ውስጡ ጉልበት አለው
ስሙ አንበሳ ነው የሚያስፋራ ስም ነው