እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ (Egziabhier Teleq Neh) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ
(Liela Liela Liela)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 7:20
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

በዕውቀትህ ፡ ቀላያት ፡ ተቀደዱ
በማስተዋልህ ፡ ሰማያት ፡ ጸኑ
ጥበብህ ፡ ምድርን ፡ መሠረተ
ደመና ፡ ጠልን ፡ አንጠበጠበ

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
እግዚአብሔር ፡ ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
እግዚአብሔር

አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ በመጀመሪያ ፡ ሰማይንና ፡ ምድርን ፡ የፈጠርከው
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ብርሃንን ፡ ደግሞ ፡ ከጨለማ ፡ የለየኸው
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጠፈሩን ፡ ሰማይ ፡ የብሱንም ፡ ምድር ፡ ብለህ ፡ የጠራኸው
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ የምድርን ፡ ባዶነት ፡ በቃልህ ፡ የሞላኸው

ይሁን ፡ ይሁን ፡ ብለህ ፡ ፈጥረህ ፡ በሙሉ ፡ የሆኑልህ
እንደተናገርከው ፡ የሆነ ፡ እንዳሰብከው ፡ የቆመልህ

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
እግዚአብሔር ፡ ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
እግዚአብሔር

በዕውቀትህ ፡ ቀላያት ፡ ተቀደዱ
በማስተዋልህ ፡ ሰማያት ፡ ጸኑ
ጥበብህ ፡ ምድርን ፡ መሠረተ
ደመና ፡ ጠልን ፡ አንጠበጠበ

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
እግዚአብሔር ፡ ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
እግዚአብሔር

አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ተራሮችንም ፡ ኮረብቶችንም ፡ በሚዛን ፡ የመዘንከው
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ የምድርን ፡ አፈር ፡ በመስፈሪያ ፡ የሰበሰብከው
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ከጥንት ፡ ጀምሮ ፡ በምድር ፡ ክበብ ፡ ላይ ፡ የተቀመጥከው
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ አማካሪ ፡ አትፈልግ ፡ ጥበብህ ፡ ቁጥር ፡ የሊለው

ይሁን ፡ ይሁን ፡ ብለህ ፡ ፈጥረህ ፡ በሙሉ ፡ የሆኑልህ
እንደተናገርከው ፡ የሆነ ፡ እንዳሰብከው ፡ የቆመልህ

ንግስናና ፡ ክብርን ፡ የለበስህ
በማስተዋል ፡ እጅቅ ፡ ድንቅ ፡ የሆንህ
ሃሳብህ ፡ ጥልቅ ፡ የማይመረመር
ካልኩት ፡ በላይ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
እግዚአብሔር ፡ ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
እግዚአብሔር

አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ፍጥረት ፡ በሙሉ ፡ በፊትህ ፡ ወድቆ ፡ የሚሰግድልህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ እኩያ ፡ አምሳያ ፡ የለህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ምንም ፡ ነገር ፡ ሳይኖር ፡ ከሁሉ ፡ በፊት ፡ ብቻህን ፡ የነበርከው
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ሁሉመ ፡ ነገር ፡ ሲያልፍ ፡ ሲጠቀለል ፡ የምትኖረው

ታዲያ ፡ ይህን ፡ ሁሉ ፡ ያየ ፡ አትኩሮ ፡ ያስተዋለ
ትልቅ ፡ ነህ ፡ ከማለት ፡ በቀር ፡ የሚለው ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
እግዚአብሔር ፡ ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
እግዚአብሔር

ንግስናና ፡ ክብርን ፡ የለበስህ
በማስተዋል ፡ እጅቅ ፡ ድንቅ ፡ የሆንህ
ሃሳብህ ፡ ጥልቅ ፡ የማይመረመር
ካልኩት ፡ በላይ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር

እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
እግዚአብሔር ፡ ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ
እግዚአብሔር