ብቻውን ፡ ይችላል (Bechawen Yechelal) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

Liela Liela Liela
(Liela Liela Liela)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

የታል እስኪ የታል በስራ ሚበልጠው እስኪ ይነሳ የታል
የታል እስኪ የታል በዝና ሚበልጠው እስኪ ይነሳ የታል

ጌታ እኩያ የለህም
አንተ መተኪያ የለህም

ዙፋን ላይ ብቻውን በሰማይ ብቻውን
ግዛቱ ብቻውን ስልጣኑ ብቻውን

ብቻውን እርሱ ብቻውን/4

ለየት ያለ ጌታ አቻ ያልተገኘለት
የሰማይ የምድሩ ፈጠራ ባለቤት
እርሱ በፈጠረው መቼ ሌላ ያዛል
መልክ መልክ አሲዞ ያሻውን ያረጋላ

ያረጋላ ብቻውን ያረገዋል
ያረጋላ እየስይስ ያረገዋል
ይችላህ ብቻውን ይችላዋል
ይችላህ አምላኬ ይችላዋል

ሲሰለፍ ብቻውን ሲዋጋ ብቻውን
ሲረታ ብቻውን ሲያሸንፍ ብቻውን

ብቻውን እርሱ ብቻውን/4

እንዳንተ እንዳንተ ጌታ
ማን አለ ሁሉን የረታ
እንዳንተ እንዳንተ እየሱስ
ማን አለ የፀና ንጉስ

የታል እስኪ የታል በስራ ሚበልጠው እስኪ ይነሳ የታል
የታል እስኪ የታል በዝና ሚበልጠው እስኪ ይነሳ የታል

ጌታ እኩያ የለህም
አንተ መተኪያ የለህም

ሲሰራ ባይገባ እንዴት አይባልም
እርሱ ይመርምር እንጂ አይመረመርም
ምድርን ሲሞላ ሰማይን ሲያፀና
ያማከረው የለም ብቻውን ገናና

ገናና ብቻውን ገናና ነው
ገናና ንጉሴ ገናና ነው
ገናና ብቻውን ገናና ነው
ገናና እየሱስ ገናና ነው